አንድ ቀን እናቴ በጣም ብዙ ፍራፍሬዎች አመጣች።
有一天,妈妈买了很多水果。
መቼ ነው ታዲያ ከፍራፍሬው የምትሰጭን? ብለን ጠየቅን። ‹‹ፍራፍሬውን ማታ እንበላዋለን።›› አለች እማ።
我们都问她:“什么时候可以吃水果?”妈妈说:“等今天晚上再吃。”
ወንድሜ ራሂም ስግብግብ ነው። ከሁሉም ፍራፍሬ ቀመሰ። አብዛኛውንም እሱ በላው።
我哥哥拉希姆很贪吃,所有的水果都想尝尝。结果他吃了很多。
‹‹እዩ እዩ ራሂም ምን እንዳደረገ!›› ታናሹ ወንድሜ ጮኸ። ‹‹ራሂም ክፉ እና ራስ ወዳድ ነው›› አልኩ እኔ።
弟弟叫着说:“看看拉希姆做了什么!”。我跟着说:“拉希姆很调皮很自私。”
እኛም በራሂም ተናደንበታል። ነገር ግን ራሂም ምንም አልመሰለውም።
我们也对拉希姆很生气。可是拉希姆并不感到惭愧。
‹‹ራሂምን አትቀጭውም?›› ሲል ትንሹ ወንድሜ ጠየቀ።
小弟弟问:“拉希姆不是该罚了吗?”
‹‹ራሂም፣ ቶሎ ብለህ ይቅርታ ጠይቅ›› እናታችን አስጠነቀቀችው።
妈妈警告说:“拉希姆,你很快就会后悔的。”
‹‹ሆዴን በጣም አመመኝ›› በማለት ራሂም አልጎመጎመ።
拉希姆小声说:“我肚子很疼。”
እናታችን ይህ ሊከሰት እንደሚችል ታውቅ ነበር። ፍራፍሬው ራሂምን እየቀጣው ነው።
妈妈早料到会发生这样的事情。拉希姆受到了水果的惩罚!
በኋላም ራሂም ይቅርታ ጠየቀን። ‹‹ከእንግዲህ ዳግመኛ ስግብግብ አልሆንም›› በማለት ቃል ገባ። ሁላችንም አመንነው።
后来,拉希姆跟我们道歉说:“以后我再也不会贪吃了。”而我们这次都相信他!