አንዲስዋ ወንዶች ልጆች ኳስ ሲጫወቱ እየተመለከተች ነው። ከልጆቹ ጋር ተቀላቅላ መጫወት ፈለገች። አሰልጣኙንም ከልጆቹ ጋር እግር ኳስ ልምምድ መስራት ትችል እንደሆነ ጠየቀችው።
安迪斯瓦喜欢看男孩子们踢足球,她多么希望自己也能加入他们啊!她跑去问教练,自己能不能跟男孩们一起训练。
አሰልጣኙ እጆቹን ወገቡ ላይ አደረገ። ‹‹በዚህ ት/ቤት ወንድ ልጆች ብቻ ናቸው እንዲጫወቱ የተፈቀደላቸው፣›› አለ።
教练两手叉着腰,摇了摇头说:“在这个学校,只有男孩们能踢足球。”
ልጆቹ ሄዳ ‹‹ኔት ቦል›› እንድትጫወት ነገሯት። እነሱም ለሴት ‹‹ኔት ቦል›› እንደሆነ፣ እግር ኳስ ግን ለወንድ ልጆች እንደሆነ ነገሯት። አንዲስዋ ተናደደች።
男孩们让安迪斯瓦去玩投球。他们觉得,女孩们应该玩儿投球,足球是男孩们的运动。安迪斯瓦很沮丧。
በሚቀጥለው ቀን ት/ቤቱ ታላቅ የአግር ኳስ ግጥሚያ ነበረበት። አሰልጣኙ በጣም ተጨንቋል፤። ምክንያቱም የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች በህመም ምክንያት መጫወት ባለመቻሉ ነበር።
第二天,学校里要举行一场盛大的足球比赛。教练有点儿担心,因为队里最棒的球员生病了,没法上场。
አንዲስዋ ወደ አሰልጣኙ እየሮጠች ሄዳ እንድትጫወት እንዲፈቅድላት ለመነችው። አሰልጣኙ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገባው። ከዚያም አንዲስዋ ቡድኑን እንድትቀላቀል ፈቀደላት።
安迪斯瓦跑到教练那里,求他让自己替补上场。教练犹豫不决,最后他决定让安迪斯瓦试一试。
ጨዋታው በጣም ፈታኝ ነበር። በመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ማንም ጎል ሊያስቆጥር አልቻለም።
比赛很激烈,半场结束后,两队都没有进球。
በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታው ጊዜ፤ ከልጆቹ መካከል አንዱ ኳስ ለአንዲስዋ አቀበላት። ኳሱን በፍጥነት ወደ ጎል እያንከባለለች ሄደች። ከዚያም ኳሱን በኃይል አክርራ መታችውና ጎል አስቆተረች።
比赛的下半场,一个男孩把球传给安迪斯瓦,安迪斯瓦飞快地朝球门跑去,用力一踢,球进了!
ተመልካቹ በደስታ አበደ። ከዚያ ቀን ጀምሮ ሴቶችም በት/ቤቱ ኳስ እንዲጫወቱ ተፈቀደላቸው።
人群沸腾了!从那天开始,女孩们也可以在学校踢足球了。