አንድ ቀን ጥንቸል በወንዝ ዳር እየሄደች ነበር።
有一天,兔子在河边散步。
ጉማሬም እዚያው ነበር። እየተንሸራሸረና ጥሩ ለምለም ሳር እየበላ ነበር።
河马也在那儿,一边闲逛,一边找些美味的野草来吃。
ጉማሬ ጥንቸልን አላያትም ነበርና ድንገት እግሯን ረገጣት። ጥንቸልም በጉማሬ ላይ መጮህ ጀመረች። ‹‹አንተ ጉማሬ! እግሬ ላይ እንደቆምክበት አይታይህም?››
河马没有看见兔子,她不小心踩到了兔子的脚。兔子尖叫了一声,朝着河马大喊:“该死的河马!没看到你踩到我的脚了吗?”
ጉማሬም ጥንቸልን ይቅርታ እንድታደርግለት ጠየቃት። ‹‹ይቅርታ። አላየሁሽም እኮ። እባክሽ ማሪኝ!›› አላት። ጥንቸል ግን አልሰማም ብላ ጮኸችበት። ‹‹አውቀህ ነው ያደረከው! አንድ ቀን አሳይሃለሁ! ዋጋህን ታገኛለህ!›› አለችው።
河马赶紧给兔子道歉:“真不好意思,我的朋友!我没看见你!请原谅我!”兔子哪里会听河马的解释,他气极了,朝着河马大吼:“你肯定是故意的!总有一天你会受到惩罚!”
ጥንቸል እሳትን ፈልጋ ሄደችና ስታገኛት ‹‹ሂጂ፣ ጉማሬ ከውኃ ውስጥ ሳር ሊግጥ ሲወጣ አቃጥዪው። እግሬን አይረግጠኝ መሰለሽ!›› አለቻት። እሳትም ‹‹ችግር የለም ጥንቸል ወዳጄ። ያልሽኝን እፈጽምልሻለሁ›› አለቻት
兔子找到了火,他对火说:“趁河马从水里出来吃草的时候,朝她放一把火。她竟敢踩我的脚。”火回答说:“没问题,我的朋友!我这就按你说的做。”
በኋላም ጉማሬ ከወንዙ ርቃ ሳር ስትግጥ ‹‹ውሽ!›› ብላ እሳት ከተፍ አለችባት። ነበልባሉ የጉማሬን ጸጉር ያቃጥለው ጀመር።
过了一会儿,河马正在离河岸很远的地方吃草。呼的一声,火突然烧起来了,烧到了河马的身上。
ጉማሬ እየጮኸ ወደ ውኃ ሮጠ። ጸጉሩ በሙሉ በእሳት ተቃጠለ። ጉማሬ ማልቀስ ቀጠለ። ‹‹ጸጉሬን እሳት አቃጠለብኝ! ጸጉሬ በሙሉ አለቀ! ቆንጆ ጸጉሬን!››
河马尖叫着,赶紧跑向河边,但是她的毛发已经全部烧毁了。河马伤心地说:“我的毛都被火烧掉了!你烧了我的毛!它们全都不见了!我美丽的毛!”
ጥንቸል የጉማሬ ጸጉር በመቃጠሉ ተደሰተች። እና እስካሁን እሳትን ፍራቻ ጉማሬ ከውኃ ርቆ አይሄድም።
兔子终于报了仇,他高兴坏了;直到现在,河马也不敢离河岸太远,因为她害怕又要被火烧。