ፍየል፣ ዉሻና ላም ጥሩ ጓደኛሞች ነበሩ። አንድ ቀን በታክሲ ጉዞ ለማድረግ ተነሱ።
山羊、野狗、和水牛是很要好的朋友。有一天,他们一起坐出租车。
ከጉዟቸው መጨረሻ ሲደርሱም ታክሲ ነጂው መሳፈሪያቸውን እንዲከፍሉ ጠየቃቸው። ላም የራሷን ሒሳብ ከፈለች።
当他们到了目的地的时候,司机叫他们交车费。水牛把她自己的那份交了。
ዉሻ ትንሽ ተጨማሪ ከፈለች፤ ምክንያቱም ትክክለኛው ዓይነት ገንዘብ ስላልነበራት ነው።
野狗没有带零钱,所以他就多给了一点儿。
ሹፌሩ ለዉሻው መልስ ሊሰጣት ሲል ፍየል ምንም ሳትከፍል ሮጠች።
司机正要找钱给野狗,没想到山羊没有给钱就跑掉了。
ሹፌሩ በጣም ስለተናደደ ለዉሻ ምንም መልስ ሳይሰጣት ሄደ።
司机很生气,结果他没有给野狗找钱就开走了。
ለዚያ ነው ዛሬ ድረስ ዉሻ መኪና በመጣ ቁጥር እየሮጠች መልሷን ያልሰጣትን ሹፌር ፍለጋ ወደ መኪናው ውስጥ ለማየት የምትሞክረው።
所以,现在你可以看到野狗看到车子就拼命追上去,因为他想叫司机给他找钱。
ፍየል የመኪና ድምጽ ስትሰማ ትሮጣለች። ምክንያቱም ሂሳብ ስላልከፈለች እንዳትታሰር ስለምትፈራ ነው።
山羊呢,一听到有车来就吓得赶快逃走,因为她怕没交车费被人抓起来。
ላም ግን መኪና ሲመጣ ምንም አትጨናነቅም። መንገድም ስታቋርጥ ተረጋግታ ነው፤ ምክንያቱም ሂሳብ የለባትማ።
可是水牛听到车来一点儿都不急。她不慌不忙地过马路,因为她知道她已经把她自己那份交了。