下载 PDF
返回故事列表

አህያ ሆኖ የተወለደው ልጅ 驴孩子

作者 Lindiwe Matshikiza

插图 Meghan Judge

译文 Dawit Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 3级

将整故事念出来

播放速度

自动念故事


አንዲት ህጻን ልጅ አንድ የሆነ አስገራሚ ቅርጽ ከርቀት ተመለከተች።

有个女孩最先发现了远处有个奇怪的身影。


ያ ቅርጽ እየቀረበ ሲመጣ ድርስ እርጉዝ ሴት መሆኗን ህጻኗ ተረዳች።

那个身影越靠越近,她看清楚了,那是一个快生孩子的妇女。


ዓይንአፋር ግን ደግሞ ጎበዝ የሆነችው ይህች ህጻን እርጉዟን ሴትዮ ተጠጋቻት። ‹‹ይህችን ሴት ከእኛ ጋር ማኖር አለብን›› በማለት የህጻኗ ቤተ ዘመዶች ወሰኑ። ‹‹እሷን ከእኛ ጋር እናኖራታለን፤ ልጇንም አንንከባከባለን።››

女孩有点儿害羞,但她还是勇敢地走上前去。和女孩随行的人们说:“我们必须和她呆在一起,我们必须保护她和她的孩子。”


ወዲያው ምጥ ጀመራት። ‹‹ግፊ!›› ‹‹ብርድ ልብስ አምጡ!›› ‹‹ውሃ!›› ‹‹ግፊፊፊፊፊፊ!!!››

孩子很快就要降生了。“用力啊!”“快拿毯子来!”“水!”“再用点力!”


ነገር ግን ህጻኑን ሲያዩ ሁሉም በድንጋጤ ወደኋላ አፈገፈጉ። ‹‹አህያ?!››

当他们看到孩子时,所有人都吓了一跳,“一头驴?”


ሁሉም መከራከር ያዘ። ‹‹እናትና ልጇን እንንከባከባለን ብለን ቃል ገብተን ነበር፤ አሁንም ቢሆን ማድረግ ያለብን እሱን ነው።›› ሲሉ አንዳንዶቹ፤ ሌሎቹ ደግሞ ‹‹ግን መጥፎ እድል ሊያመጡብን ይችላሉ›› አሉ።

大家七嘴八舌吵起来。一些人说:“我们说过要保护母亲和孩子的,我们必须这样做。”但是还有一些人反驳说:“但是他们会给我们带来厄运。”


በመሆኑም ሴትዮዋ እንደገና ብቸኝነት ተሰማት። ሴትዮዋ ግራ ተጋባች፤ ይህንን ያልተጠበቀ ፍጡር ምን እንደምታደርገው ጨነቃት። ምን ማድረግ እንዳለባት አላወቀችም፣ በጣም ተወዛገበች።

妇女发现自己又孤零零一人了。她不知道该拿这个奇怪的孩子怎么办,她也不知道自己该怎么办。


በስተመጨረሻም ፍጡሩ ልጇ መሆኑንና እሷም እናቱ መሆኗን አምና ተቀበለች።

最后,她决定接受这个孩子,做他的妈妈。


አሁን ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ እየሆኑ መጥተዋል። ልጁ እንደተወለደ ባለው የአካል መጠን በዚያው ቢቀጥል ልዩ ነገር ነው የሚሆነው። ሲያድግም ለናትየዋ ለመንከባከብ፣ ለማዘል ይቸግራታል። የሆነ ሆኖ ህጻኑ አህያ ለእናትየዋ በጀርባዋ ማዘል እስኪያቅታት ድረስ እያደገ መጣ። እናም ልጁ የጣረውን ያህል ቢጥር ልክ እንደሰው ያለ ባህርይ ሊኖረው አልተቻለውም። እናትየዋም እየደከማት እየፈራችም መጣች። አንዳንዴ እንስሳት እንደሚሰሩት ያለ ስራ እንዲሰራ ታደርገዋለች።

如果这个孩子一直这般大小,不长大的话,一切都会变得不一样。但是这个驴孩子越长越大,现在他再也不能趴在妈妈的背上。无论他多么努力,他始终不能像人类一样。他的妈妈累了,放弃了。有时候,她让他做一些动物会做的工作。


አህያው በውስጡ ግራ መጋባትና ብስጭት እያየለበት መጣ። ይህንና ያንን ማድረግ ላይኖርበት ይችላል፤ እንደዚህ መምሰል እንደዛም መምሰል አይኖርበትም። በዚህ መወዛገብ ውስጥ ሆኖ ይናደዳል፤ አንድ ቀን እናቱን በርግጫ መታትና ከመሬት ጋር አጋጫት።

驴孩子感到迷茫,也很生气。他这个也不能做,那个也不能做。他不能这样,也不能那样。有一天,他太生气了,一脚把他的妈妈踹到地上。


አህያው በጣም ሃፍረት ተሰማው። ከዚያ ሮጠ። የሚችለውን ያህል ፈጥኖ በጣም ሩቅ ወደሆነ ቦታ ፈረጠጠ።

驴孩子羞愧极了,他逃跑了,跑得越远越好。


መሮጡን ሲያቆም መሽቶ ነበር፣ በዚህም አጋጣሚ አህያው ጠፋ። ‹‹ሃ ሂሃ ሂሃ›› አህያው ጨለማው ውስጥ አስካካ። ‹‹ሃ ሂሃ ሂሃ›› ይላል ደግሞ። ግን የገደል ማሚቶው ብቻ ያስተጋባል። ብቻውን ሆነ። ከባድ የድካም ስሜት እንደተጫነው ጥቅልል ብሎ ተኛ።

当他停下来的时候,天已经黑了,驴孩子迷路了。他在黑暗里哼哼,“咴咴”,黑暗中传来了回声,“咴咴”。他孤零零的一个人,卷成了一团,心中充满烦恼,沉沉地睡去。


አህያው ሲነቃ እንግዳ ሽማግሌ ሰውዬ አፍጥጦ ሲያየው አገኘ። ሽማግሌውን ዓይን ዓይኑን እያየ የተስፋ ጭላንጭል ተሰማው።

驴孩子醒了,他发现有个老人低头盯着他。他看着老人的眼睛,感觉到了一丝希望。


አህያው እንዴት መኖር እንደሚገባው የተለያዩ ዘዴዎችን ካስተማረው ከሽማግሌው ሰውዬ ጋር ለመቆዬት አብሮ ሄደ። አህያው በደንብ ያዳምጣል። ትምህርት ይወስዳል። ሽማግሌው ሰውዬም እንደዚያው። እርስበርሳቸው ይረዳዳሉ፤ ይሳሳቃሉም።

驴孩子和老人住在一起,老人教会他很多生存的本领。驴孩子认真地听着,学得很快。老人也学了很多。他们互相帮助,遇到开心的事情就一起哈哈大笑。


አንድ ቀን ማለዳ ሽማግሌው ሰውዬ አህያውን ተሸክመህ ወደ ተራራ ጫፍ አውጣኝ ሲል ጠየቀው።

一天早上,老人让驴孩子带他到山顶。


ተራራው ጫፍ ላይ በደመናው መሃል እንቅልፍ ወሰዳቸው። አህያው በህልሙ እናቱን እንዳመማትና ስትጠራው አየ። እንደነቃ….

他们登上山顶,环绕在云雾中,睡着了。驴孩子梦到他的妈妈生病了,正在呼唤他,然后他就醒了……


… ደመናው ጠፍቷል፣ ከጓደኛው ከሽማግሌው ሰውዬ ጋር።

……云雾消失了,他的朋友——那个老人——也消失了。


አህያ በስተመጨረሻም ምን ማድረግ እንዳለበት አወቀ።

驴孩子终于知道要做什么了。


አህያው እናቱን ብቻዋን ሆና በጠፋው ልጇ እያዘነች አገኛት። ለረጂም ጊዜ ፍጥጥ ብለው ተያዩ። ከዚያም ጥብቅብቅ ብለው ተቃቀፉ።

驴孩子找到了他的妈妈,她孤零零一个人,正在为走失的孩子伤心。他们互相打量了很久,然后紧紧地抱在了一起。


ትንሹ አህያና እናቱ አብረው መኖርና ማደግ ጀመሩ። ህይወታቸውን አብረው ማስቀጠል የሚችሉባቸውን በርካታ መንገዶችም አሰቡ። ቀስ በቀስ ሌሎች ሰዎችና ቤተዘመዶች ተረጋግተው ህይወታቸውን መግፋት ጀመሩ።

驴孩子和妈妈住在一起,慢慢长大,学会了如何共同生活。渐渐的,其他的家庭也搬到他们附近,住了下来。


作者: Lindiwe Matshikiza
插图: Meghan Judge
译文: Dawit Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 3级
出处: 原文来自非洲故事书Donkey Child
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 4.0 未本地化版本授权条款授权。
选项
返回故事列表 下载 PDF