下载 PDF
返回故事列表

ዶሮና ሃምሳ እግር 鸡和千足虫

作者 Winny Asara

插图 Winny Asara

译文 Dawit Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 3级

将整故事念出来

播放速度

自动念故事


ዶሮና ሃምሳ እግር ጓደኞች ነበሩ። ሁሌም ግን ይፎካከራሉ። አንድ ቀን ኳስ ለመግጠምና ማን እንደሚበልጥ ለማየት ወሰኑ።

鸡和千足虫是好朋友,但是它们又互相竞争。有一天,它们决定进行一场足球比赛,看看谁是最棒的球员。


ወደ ኳስ ሜዳ ሄዱና መጫወት ጀመሩ። ዶሮዋ ፈጣን ነበረች። ሃምሳ እግርም ግን ከሷ ይበልጥ ነበር። ዶሮ አርቃ ትለጋለች፣ ሃምሳ እግርም ከሷ አርቆ ይለጋል። ዶሮ መደካከምና መናደድ ጀመረች።

它们去了球场,开始比赛。鸡跑得飞快,但是千足虫跑得更快。鸡把球踢得很远,但是千足虫踢得更远。鸡开始有点闷闷不乐。


በፍጹም ቅጣት ምት ይዋጣልን ብለው ወሰኑ። መጀመሪያ ሃምሳ እግር በረኛ ሆነ። ዶሮ መታች፣ አንድ ጎል አገባች። በመቀጠል የሃምሳ እግር ተራ ሆነ። መምታትና ጎል አስቆጥሮ ማካካስ አለበት።

最后,它们决定来一场点球大战。第一轮中,千足虫当守门员,鸡只拿到了一分。然后,在第二轮中,鸡做守门员。


ሃምሳ እግር መታ፣ አገባ። ሃምሳ እግር አታሎ አልፎ አገባ። ሃምሳ እግር በጭንቅላቱ መታ፣ አገባ። ሃምሳ እግር አምስት ጎል አገባ።

千足虫猛地一踢,球进了。千足虫运球飞快,又进了一球。千足虫跳起来,打了个头球,又得了一分。千足虫一共得了五分。


ዶሮ በመሳቷ በጣም ተናደደች። በጣም አሳዛኝ ተሸናፊ ሆነች። ሃምሳ እግር መሳቅ መፈንደቅ ጀመረ ምክንያቱም ጓደኛውም ብትሆን እንዲህ ያለ ፈንጠዝያ ታበዛ ነበር።

鸡输了,它很生气。千足虫哈哈大笑,因为它的朋友输了球,就无理取闹。


ዶሮ በጣም ተናዳ ስለነበር አፏን ከፈተችና ሃምሳ እግርን ዋጠችው።

鸡生气极了,它张开嘴,一口把千足虫吞了下去。


ዶሮ ወደቤቷ እየሄደች ሳለ የሃምሳ እግር እናት አገኘቻት። እናትየዋ ሃምሳ እግርም ‹‹ልጄን አይተሻል?›› ብላ ጠየቀቻት። ዶሮ በበኩሏ ምንም አላለች። እናትዬዋ ሃምሳ እግር በጣም ተጨነቀች።

鸡回家的路上,遇到了千足虫妈妈。千足虫妈妈问它:“你看见我的孩子了吗?”鸡什么都没说,千足虫妈妈很担心。


ከዚያም እናትዬዋ ሃምሳ እግር ትንሽ ድምጽ ነገር ሰማች። ‹‹እርጂኝ እናቴ!›› እያለ የሚጮህ ድምጽ። እናት ሃምሳ እግር አካባቢውን እየቃኘች በጥንቃቄ አዳመጠች። ድምጹ ከዶሮዋ ውስጥ እንደሚወጣ ተረዳች።

千足虫妈妈突然听到了一阵微弱的声音:“快帮我,妈妈!”千足虫妈妈看了看周围,仔细地听着,声音是从鸡身体里传出来的。


‹‹ልጄ ያለህን ልዩ ኃይል ተጠቀም!›› እናት ሃምሳ እግር ጮኸች። ሃምሳ እግር አስቀያሚ ሽታና አስከፊ ቃና መልቀቅ ጀመረ። ዶሮ ህመም ይሰማት ጀመር።

千足虫妈妈大喊道:“快用你神奇的能力!”千足虫会产生一种很难闻的味道,会让鸡觉得很恶心。


ዶሮ አገሳች። ከዚያ ዋጠችና ወዲያው አስታወከች። ከዚያም አነጠሰችና ሳለች። ደግማ ሳለች። ሃምሳ እግር አስጠሊታ ነበር!

鸡打了一个嗝,咕噜咕噜要吐了,又是打喷嚏又是咳嗽。千足虫太恶心了!


ዶሮ በሆዷ ውስጥ ያለው ሃምሳ እግር እስኪወጣ ድረስ አሳላት። ተፈትልኮ ወጣ። ከዚያም እናትዬዋ ሃምሳ እግርና ልጇ ወደዛፉ ላይ ወጥተው ተደበቁ።

鸡不停地咳嗽,直到把千足虫从胃里咳了出来。千足虫妈妈和孩子赶紧爬上树,藏了起来。


ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዶሮዎችና ሃምሳ እግሮች ጠላቶች ሆኑ።

从此以后,鸡和千足虫就变成了敌人。


作者: Winny Asara
插图: Winny Asara
译文: Dawit Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 3级
出处: 原文来自非洲故事书Chicken and Millipede
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 3.0 未本地化版本授权条款授权。
选项
返回故事列表 下载 PDF