下载 PDF
返回故事列表

አናንሲና ጥበብ 阿南西和智慧

作者 Ghanaian folktale

插图 Wiehan de Jager

译文 Mezemir Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 3级

将整故事念出来

播放速度

自动念故事


በድሮ ዘመን ሰዎች ምንም አያውቁም ነበር። ሰብል እንዴት እንደሚዘራ፣ ሽመናም ሆነ የአንጥረኝነት ስራ እንዴት እንደሚሰራ ምንም ሃሳብ አልነበራቸውም። በሰማይ ያለው ንያሜ የተባለው አምላክ ግን የዓለምን ሁሉ ጥበብ ይዞ ነበር። በአንድ ገንቦም ውስጥ በጥንቃቄ አስቀምጦት ነበር።

很久很久以前,人们什么都不知道。 他们不知道怎么耕田织布,也不知道怎么制造铁器。 天上的尼亚美神把世界所有的智慧都藏在一个砂锅里面。


ከዕለታት አንድ ቀን ንያሜ ይህን የዕውቀት ገምቦ ለአናንሲ ለመስጠት ወሰነ። አናንሲ የሸክላውን ገንቦ ባየ ቁጥር አንድ አዲስ ነገር ያገኝ ነበር። ያስደስት ነበር!

有一天,尼亚美决定把藏有智慧的砂锅交给蜘蛛神阿南西。 每当阿南西揭开砂锅往里看,他就会学到新的东西。他感到很兴奋!


ገብጋባው አናንሲ ‹‹ይህን ገንቦ በአንድ ትልቅ ዛፍ ጫፍ በጥንቃቄ አስቀምጠዋለሁ። ከዚያም ሁሉም የኔው ይሆንልኛል!›› ሲል አሰበ። አንድ ረጅም ክርም ገምዶ በሸክላው ገንቦ ዙሪያ አሰረ፤ ከዚያም በሆዱ ዙሪያ ጠመጠመ። ዛፉንም መውጣት ጀመረ። ገንቦው አሁንም አሁንም ጉልበት ጉልበቱን እየመታው ዛፍ መውጣቱ ከበደው።

贪心的阿南西跟自己说, “我把砂锅安放在树顶上,那样所有的智慧就都只属于我了!” 所以,他织出了一条长长的丝线,把砂锅牢牢地拴住,然后把丝线的另一端系在自己的肚子上。 他开始往那棵树上爬, 可是砂锅总是撞到他的腿,爬起来很辛苦。


ይህን ሁሉ ጊዜም የአናንሲ ትንሽ ልጅ ከዛፉ ስር ቆሞ እየተከታተለው ነበር። እሱም ‹‹አዝለኸው ብትወጣ አይሻልም ወይ?›› አለው። አናንሲ ጥበብ የያዘውን የሸክላ ገንቦ ከጀርባው ለማሰር ሞከረ፤ እውነትም አመቺ ነበር።

阿南西的儿子在树底下看到了一切。 他跟阿南西说,“把砂锅扛在背上不就容易了吗?” 于是阿南西就试着把砂锅扛在背上,果然容易很多。


ባጭር ጊዜም ከዛፉ ጫፍ ደረሰ። እዚያም ቆም አለና ‹‹ይህ ሁሉ ዕውቀት የኔ እንዲሆን ነው የተፈለገው፤ ግን ይሄው ልጄ ከኔ የበለጠ ብልህ ሆነ!›› በማለት አሰበ። አናንሲ በዚህ በጣም ተናዶ ያንን የሸክላ ገንቦ ከዛፉ ላይ ወደ ታች ወረወረው።

阿南西很快就爬到树顶上。 可是他突然想到一个问题: “拥有所有智慧的人应该是我,可是刚才我儿子居然比我还聪明!” 阿南西气得差点跳起来了,一气之下竟把砂锅扔到树下。


መሬትም ላይ ወድቆ ፍርክስክሱ ወጣ። ጥበብም ለማንኛውም ሰው በእኩል ተዳረሰ። በዚህም ምክንያት ነበር ሰዎች እርሻ፣ ሽመና፣ አንጥረኝነትና ሌሎችንም ሰዎች መስራት የሚችሏቸውን ነገሮች ሁሉ የተማሩት።

砂锅一落地就碎成小片。 砂锅碎了,所有的智慧也跑了出来,大家可以自由分享了。 就是这样,世上的人们才学会如何耕田、如何织布,如何打铁做铁器,还有所有现在人会做的一切。


作者: Ghanaian folktale
插图: Wiehan de Jager
译文: Mezemir Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 3级
出处: 原文来自非洲故事书Anansi and Wisdom
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 3.0 未本地化版本授权条款授权。
选项
返回故事列表 下载 PDF