下载 PDF
返回故事列表

ትንሽ ዘር፣ የዋንጋሪ ማታይ ታሪክ 一粒小种子:旺加里·马塔伊的故事

作者 Nicola Rijsdijk

插图 Maya Marshak

译文 Mezemir Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 3级

将整故事念出来

播放速度

自动念故事


በምስራቅ አፍሪካ በሚገኘው የኬንያ ተራራ በአንድ በኩል በሚገኝ አንድ መንደር አንዲት ትንሽ ልጅ ከእናቷ ጋር በማሳ ላይ ትሰራ ነበር። ስሟም ዋንጋሪ ይባላል።

在东非肯尼亚山的山腰上,有一座小村庄,村庄里有一个小女孩和妈妈一起在田里劳作,这个女孩叫旺加里。


ዋንጋሪ ውጪ ውጪውን ማለት ትወዳለች። በቤተሰቧ የአትክልት ስፍራ አፈሩን በገጀራ ትቆፍራለች። ትናንሽ ዘሮችንም ወደ ሞቃቱ መሬት ትከታለች።

旺加里很喜欢呆在户外。在她家的农田里,旺加里用弯刀劈开土地,把小种子播撒到温暖的泥土里。


ፀሐይ ከገባች በኋላ ያለውን ጊዜ በጣም ትወደዋለች። እጽዋቱ አልታይ ማለት በሚጀምሩበት ጊዜ ዋንጋሪ ወደ ቤቷ መሄጃው ሰዓት መድረሱን ታውቃለች። በማሳዎቹ ውስጥ ያሉትን ጠባብ መንገዶች ተከትላና ስትሄድ እንዳደረገችው ወንዙን አቋርጣ ትመለሳለች።

她一天中最喜欢的时候就是日落时分。当天黑了,看不到花花草草时,旺加里就知道她该回家了。她走在农田里的小路上,还要过几条河。


ዋንጋሪ ትምህርት ቤት መሄድ የምትወድ ጎበዝ ልጅ ነበረች። እናትና አባቷ ግን እቤት ቆይታ እንድታግዛቸው ይፈልጉ ነበር። ሰባት ዓመት ሲሆናት ታላቅ ወንድሟ ወላጆቿን ትምህርት ቤት እንዲያስገቧት አሳመናቸው።

旺加里是个聪明的孩子,她迫不及待地想要去上学,但是她的父母希望她能在家,帮着干农活。当旺加里七岁的时候,她的哥哥说服了父母,让旺加里去上学。


ዋንጋሪም ትምህርት ትወድ ነበር! መጽሐፍ ባነበበች ቁጥር ብዙ እያወቀች መጣች። በትምህርቷ ጥሩ ውጤት ስላስመዘገበች አሜሪካ እንድትማር ተጋበዘች። ዋንጋሪ እጅግ ተደሰተች! ስለ ዓለም ብዙ ለማወቅም ፈለገች።

旺加里太喜欢学习了。旺加里读了很多书,学到很多知识。她的成绩非常好,最后收到了美国大学的录取信,邀请她去美国读书。旺加里太兴奋了,她真想去世界各地走走看看。


በአሜሪካውም ዩኒቨርሲቲ ዋንጋሪ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ተማረች። እጽዋትንና አስተዳደጋቸውን ተማረች። ራሷ እንዴት እንዳደገችም አስታወሰች። በሚያማምሩት የኬንያ ደኖች ከወንድሞቿ ጋር የተለያዩ ጨዋታዎችን ስትጫወት ነበር ያደገችው።

在美国的大学里,旺加里学到了很多新鲜事物。她研究植物,以及它们的生长过程。她想起她自己是怎么长大的:她和兄弟们在美丽的肯尼亚森林里玩耍。


ብዙ እየተማረች ስትሄድም የኬንያን ህዝብ መውደዷ የበለጠ እየተገለጠላት መጣ። ደስተኛና ነጻ ሕዝብ እንዲሆን ፈለገች። ብዙ እየተማረች ስትሄድም የአፍሪካው ቤቷ ይበልጥ ትዝ እያላት መጣ።

她学得越多,就越热爱肯尼亚人民。她想要帮助肯尼亚人民过上自由、快乐的生活。她学得越多,就越想念自己在非洲的家乡。


ትምህርቷን ስትጨርስ ወደ ኬንያ ተመለሰች። አገሯን ግን ተቀይራ አገኘቻት። ትላልቅ እርሻዎች አገሪቱን አጥለቅልቀዋታል። ሴቶች ለማገዶ የሚሆን እንጨት አልነበራቸውም። ህዝቡ ደህይቶ ልጆቹ ተርበዋል።

当旺加里完成学业时,她回到了肯尼亚,但是她的祖国已经今非昔比了。大地上建起了农场,妇女们找不到柴火做饭。人们过着穷苦的日子,孩子们饥肠辘辘。


ዋንጋሪ ምን ማድረግ እንዳለባት ታውቅ ነበር። ሴቶቹን ችግኝ እንዴት እንደሚያቸግኑና ዛፍ እንዴት እንደሚተክሉ አስተማረቻቸው። ሴቶቹም ዛፎቹን እየሸጡ ቤተሰባቸውን ማስተዳደር ቻሉ። ሴቶቹ በጣም ተደሰቱ። ዋንጋሪ አቅም እንዳላቸው እንደዲገነዘቡ ረድታቸዋለች።

旺加里知道自己要做什么。她教妇女们如何用种子种出大树。妇女们卖树赚钱,补贴家用。妇女们都很高兴。旺加里使她们觉得自己变得坚强勇敢了。


ከረጅም ጊዜ በኋላም አዳዲሶቹ ዛፎች ደን ሆኑ፤ ወንዞቹም እንደዱሮው መፍሰስ ጀመሩ። የዋንጋሪም መልዕክት በመላው አፍሪካ ተሰራጨ። ዛሬ ከዋንጋሪ ዘሮች ብዙ ዛፎች ተገኝተዋል።

时光飞逝,小树长成了参天大树,又汇聚成了森林,河水穿流而过。旺加里的办法传遍了非洲。今天,因为旺加里当初的种子,已经长出了几百万棵大树。


ዋንጋሪ በጣም ለፍታለች። በዓለም ዙሪያ የነበሩ ሰዎች ስራዋን አይተው ትልቅ ሽልማት ሰጧት። የዓለም የኖቤል ሽልማት ይባላል ሽልማቱ። ዋንጋሪም ይህን ሽልማት ስትቀበል የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሴት ነች።

旺加里努力工作,引起了全世界的注意,人们授予她诺贝尔和平奖,她是非洲第一位获得这份殊荣的女性。


ዋንጋሪ በ2011 አርፋለች። የሚያምር ዛፍ ባየን ቁጥር ግን ልናስታውሳት ይገባናል።

旺加里在2011年去世,但是每次我们看到大树时,都会想起这位杰出的女性。


作者: Nicola Rijsdijk
插图: Maya Marshak
译文: Mezemir Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 3级
出处: 原文来自非洲故事书A Tiny Seed: The Story of Wangari Maathai
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 4.0 未本地化版本授权条款授权。
选项
返回故事列表 下载 PDF