返回故事列表
ይህ የማር ቆራጩ መሪ የንጌዴና ግንጊሌ የተባለ ገብጋባ ወጣት ታሪክ ነው። አንድ ቀን ግንጊሌ አደን ላይ ሳለ የንጌዴን ጥሪ ሰማ። ግንጊሌ ማርን አስቦ ጎመዠ። ከራሱ በላይ ባሉት የዛፍ ቅርንጫፎች ወፉን እስኪያየው ድረስ እየፈለገ ቆም ብሎ በጥንቃቄ አደመጠ። ‹‹ችክ፣ ችክ፣ ችክ›› በማለት ወደ ቀጣዮቹ ዛፎች እየበረረ ትንሹ ወፍ ጮኸ። ግንጊሌ መከተሉን እርግጠኛ ለመሆን ቆም እያለ እያየ ‹‹ችክ፣ ችክ፣ ችክ›› እያለ ተጣራ።
这是一个关于指蜜鸟奈吉和贪婪的年轻人青其儿的故事。有一天,青其儿外出打猎,忽然,他听到了奈吉的叫声。青其儿一想到跟着指蜜鸟就能找到美味的蜂蜜,口水就忍不住流了出来。他停下来,仔细地听着,四处找寻,直到他在头上的树枝里看到了指蜜鸟。小鸟啾啾啾地叫着,从一根树枝飞到另一个树枝。指蜜鸟一边飞一边叫,让青其儿能跟上它。
ከግማሽ ሰዓት በኋላ ከአንድ ትልቅ ሾላ ጋ ደረሱ። ንጌዴ በቅርንጫፎቹ መካከል የሚያደርገውን አጥቶ ቱር ቱር አለ። ካንዱም ቅርንጫፍ ላይ ተረጋግቶ ራሱን ወደ ግንጊሌ ዘንበል አድርጎ ‹‹ይሄውና! አሁን ና! ይህን ያህል ምን አቆየህ?›› የሚለው መሰለ። ግንጊሌ ከዛፉ ስር ምንም ንቦች አልታዩትም፤ ንጌዴን ግን አምኖታል።
过了大概半个小时,他们到了一棵巨大的野无花果树下。奈吉在树枝间跳来跳去,然后在其中一根树枝上停了下来,它朝青其儿伸出脑袋,好像在说:“就是这儿!快来!别磨磨蹭蹭的。”青其儿站在树下,看不到一只蜜蜂,但是他相信奈吉不会骗他。
ስለዚህ ግንጊሌ የማደኛ ጦሩን ከዛፍ ስር አስቀምጦ ደረቅ እንጨቶችን ለቀመና እሳት አቀጣጠለ። እሳቱ በደንብ ሲቀጣጠል አንድ ረጅም ደረቅ እንጨት በእሳቱ መካከል አደረገ። ይህም እንጨት ሲነድ ብዙ ጭስ የሚወጣው ዓይነት ነበር። በእሳት ያልተያያዘውን የእንጨቱን ጫፍ በጥርሱ ይዞ ዛፍ ይወጣ ጀመር።
青其儿把他打猎的矛搁在树下,搜集了一些干枯的小树枝,点了一堆火。当火慢慢旺起来的时候,他拿了一根又长又干的树枝,伸向火堆中心。这种木头烧起来的时候,会释放出很多烟。青其儿一手拿着树枝的另一头,另一只手抓着树干,开始爬树。
ወዲያውኑም የንቦች ድምጽ ጎልቶ ተሰማው። በዛፉ ግንድ ላይ ካለ ቀዳዳ ነበር እየወጡ ያሉት - ከቀፏቸው። ግንጊሌም ከቀፎው ሲደርስ በመቀጣጠል ላይ ያለውን የእንጨቱን ጫፍ ወደ ቀዳዳው ጨመረው። ንቦቹም ተናደው መውጣት ጀመሩ። ጭሱንም ስላልወደዱት በረው ጠፉ፤ ግንጊሌንም ነደፉት!
不久青其儿就听到了蜜蜂飞来飞去的嗡嗡声。它们在树干里筑了一个巢,正忙着飞进去飞出来。当青其儿爬到蜂巢附近的时候,他把树枝燃烧的一端猛地戳到蜂巢里。蜜蜂们害怕灰烟,它们都吓坏了,赶紧全都飞出来,但它们没忘记给青其儿脸上、身上狠狠地叮上几口。
ንቦቹም እንደወጡ ግንጊሌ እጆቹን ወደ ቀፏቸው አስገባቸው። በጥሩ ማር የተሞላ ብዙ ከባባድ እጭም አወጣ። በትከሻውም ላይ ካነገተው ኮረጆ አስቀመጠውና ከዛፉ መወረድ ጀመረ።
蜜蜂全都飞出来了,青其儿把手伸进蜂巢里,他挖到了好多蜜块,又甜又香的蜂蜜从蜜块上滴下来,看起来美味极了。他小心翼翼地把蜂蜜块放进肩膀上的袋子里,慢慢地从树上爬下来。
ንጌዴ ግንጊሌ የሚሰራውን እያንዳንዱን ነገር በጉጉት እየተከታተለ ነበር። ለማር ቆረጣ ስለመራው በማመስገን ከያዘው ማር ትንሽ ቆረጥ አድርጎ እንዲሰጠው እየጠበቀ ነበር። ንጌዴ ከቅርንጫፍ ቅርንጫፍ ለመሬት ቀረብ ብሎ ይዘዋወር ጀመር። በመጨረሻም ግንጊሌ ከዛፉ ወረደ። ንጌዴም ከአጠገቡ ካለ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ ሽልማቱን ይጠብቅ ጀመር።
奈吉迫不及待地看着青其儿做这些事情,它等着青其儿能送它一小块蜂蜜,作为给他引路的谢礼。青其儿在树枝间轻快地跳来跳去,离地面越来越近。终于青其儿稳稳地落地,奈吉落在他附近的一块石头上,等着青其儿给他的礼物。
ግንጊሌ ግን እሳቱን አጥፍቶ፣ ጦሩን አንስቶና ወፉን ረሰቶ ወደቤቱ መሄድ ጀመረ። ንጌዴም በንዴት ‹‹ቪክ ቶር! ቪክ ቶር›› ሲል ተጣራ። ግንጊሌም ቆም ብሎ ትንሹ ወፍ ላይ አፈጠጠበትና ጮክ ብሎ ሳቀ። ‹‹ትንሽ ማር ፈለገህ ነው፣ ነው አይደል፤ ወዳጄ? አሃ! ግን ስራውን ሁሉ እኮ እኔ ነኝ የሰራሁት፤ የተነደፍኩትም እኔው ነኝ። ታዲያ ከዚህ ማር ለምን እሰጥሃለሁ?›› አለው። ነገደም ተናደደ። እንደዚህ መደረግ አልነበረበትም! መበቀል ግን አለበት።
但是青其儿把火灭了,拎起他的矛,开始向家里走去,装作看不见奈吉的样子。奈吉生气地叫着:“给我蜂蜜!给我蜂蜜!”青其儿停下来,盯着小鸟,大笑说:“我的朋友,你也想要蜂蜜,是吗?哈哈,我做了这么多事,被叮了那么多包!我为什么要跟你分享这蜂蜜?”说完,青其儿就走远了。奈吉气极了,他可从来没有被这样对待过!等着吧,它会报仇的。
አንድ ቀን በድጋሚ፣ ከብዙ ሳምንታት በኋላ ግንጊሌ ንጌዴ ማር ሊጠቁመው ሲጠራው ሰማ። ያንን ጣፋጭ ማር አስታውሶ ወፉን በጉጉት ይከተለው ጀመር። ገግንጊሌን በጫካው ጠርዝ ከመራው በኋላ ንጌዴ በአንድ እሾሃማ ዛፍ ስር ለማረፍ ቆመ። ‹‹አሃ፣›› ‹‹ቀፎው በዚህ ዛፍ ላይ መሆን አለበት›› ሲል ግንጊሌ አሰበ። እሳቱን በፍጥነት አያይዞና የሚያያዘውን እንጨት በአፉ ይዞ ዛፉን ይወጣ ጀመር። ንጌዴም ተቀምጦ ይከታተል ጀመር።
过了几个星期,青其儿又听到了奈吉的叫声。他想起来美味的蜂蜜,迫不及待地跟着指蜜鸟走了。奈吉领着青其儿走到森林边上,在一棵大树冠上停了下来。青其儿心想:“哈哈,树上肯定有蜂巢。”他迅速地生了一小堆火,拿着燃烧的树枝开始爬树。奈吉停在那儿看着这一切。
ግንጊሌ የተለመደውን የንቦች ድምጽ ለምን እንዳልሰማ እያሰበ ዛፉ ላይ ወጣ። ‹‹ምናልባት ቀፎው በጣም ጥልቅ ቦታ ላይ ይሆናል ያለው›› ሲል ለራሱ አሰበ። ወደሌላ ከፍ ወዳለ ቅርንጫፍ ላይ ወጣ። ያገኘው ነገር ግን ቀፎ ሳይሆን ፊት ለፊት የመጣችበትን ነብር ነበር! ነብሯ እንቅልፏን ሳታስበው ስላቋረጣት በጣም ተናደደች። ዓይኖቿን ጠበብ አድርጋ፣ አፏን ከፍታ፣ ትላልቅና ሹል ጥርሶቿን አገጠጠችበት።
青其儿爬着爬着,心里觉得奇怪,怎么他没有听到嗡嗡声呢?他想,蜂巢一定在树冠很深的地方。他拉着树枝,跳上树:没有蜂巢,他看到了一只豹子!豹子非常生气,因为青其儿打扰了它的美梦。豹子眯着眼睛,张开血盆大口,露出了又白又尖的牙齿。
ነብሯ ለቀም ሳታደርገው ግንጊሌ ከዛፉ በፍጥነት መውረድ ጀመረ። በፍጥነቱም የተነሳ አንዱን ቅርንጫፍ ስቶት መሬት ላይ ክፉኛ ወድቆ ቁርጭምጭሚቱ ዞረ። በተቻለው መጠን በፍጥነት እያነከሰ ሄደ። ዕድሉ ረድቶት ነብሯ እንቅልፍ ስለተጫናት አላሳደችውም። ንጌዴ፣ የማር ቆራጩ መሪ፣ በቀሉን ተበቅሏል። ግንጊሌ ም ትምህርት ቀስሟል።
青其儿没等到豹子扑向他,就飞快地爬下树。可他爬得太匆忙了,一脚没踩稳,重重地摔在地上,扭到了脚踝。他一瘸一拐地跑走了。幸好豹子还没睡醒,没有追青其儿。指蜜鸟奈吉报了仇,青其儿也学到了教训。
ስለዚህ የግንጊሌ ልጆች የንጌዴን ታሪክ ሲሰሙ ለዚያ ትንሽ ወፍ አክብሮት አላቸው። ማር በቆረጡ ቁጥር ለማር ቆራጩ መሪ ከነእጩ ብዙ ቆረጥ አድርገው መስጠታቸውን ያረጋጣሉ።
从此以后,青其儿的孩子们都听说了奈吉的故事,都非常尊重这只小鸟。他们每次收获蜂蜜的时候,都会把最大的一块留给指蜜鸟。
作者: Zulu folktale
插图: Wiehan de Jager
译文: Mezemir Girma
配音: Abenezer Chane