下载 PDF
返回故事列表

ዓመት በዓልን ከአያት ጋር 和奶奶一起过暑假

作者 Violet Otieno

插图 Catherine Groenewald

译文 Dawit Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 4级

将整故事念出来

播放速度

自动念故事


ኦዶንጎና አፒዮ ከአባታቸው ጋር ከተማ ነው የሚኖሩት። ዓመት በዓልን በጉጉት ይጠብቃሉ። ትምህርት ስለሚዘጋ ሳይሆን በዚያ አጋጣሚ አያታቸውን የማየት እድል ስለሚያገኙ ነው። የሴት አያታቸው አሳ በሚመረትበት መንደር ከትልቁ ሐይቅ አጠገብ ይኖራሉ።

欧东格、阿皮尤和他们的爸爸一起生活在城市里。他们非常期待过暑假,因为那个时候他们不用去学校,而且他们还可以去看奶奶。他们的奶奶住在一个渔村里,靠近一片很大的湖泊。


ኦዶንጎና አፒዮ በጣም ተደስተዋል ምክንያቱም እንደገና አያታቸውን ሊጎበኙ ነው። በዋዜማው ማታ ሻንጣቸውን ሸካክፈው ወደ አያታቸው ቀዬ ለሚያደርጉት ረጂም ጉዞ ተዘጋጁ። አልተኙም፤ ሌሊቱን ሙሉ ስለበዓሉ ሲያወሩ አደሩ።

欧东格和阿皮尤又要去看奶奶了,他们非常高兴。前一天晚上,他们整理好了自己的行装,准备踏上前往渔村的旅程。他们晚上睡不着,整晚都在讨论这个暑假。


በነጋታው ጠዋት በአባታቸው መኪና ሆነው ጉዞ ጀመሩ። ተራራውን እያቆራረጡ፣ የዱር እንስሳትና የሻይቅጠል ማሳዎችን አልፈው እየሄዱ ነው። የሚያልፉ መኪናዎችን እየቆጠሩ፣ መዝሙር እየዘመሩ ነው የሚሄዱት።

第二天凌晨,他们坐着爸爸的车前往那个渔村。他们开过了山丘,路上看到了很多野生动物,经过了几个茶园。他们唱着歌数着路上的车辆。


ከጊዜ በኋላ ልጆቹ ደከማቸውና ተኙ።

过了一会儿,孩子们累了,就在车里睡着了。


ከመንደሯ ሲደርሱ አባታቸው ቀሰቀሳቸው። አያታቸው እመት ንያር ካንያዳ ዛፍ ጥላ ስር ምንጣፍ ላይ ቁጭ ብላ ረፍት ስታደርግ አገኟት። ጠንካራና ቆንጆ ሴትዮ ናት።

当他们到达那个渔村的时候,爸爸把欧东格和阿皮尤叫醒了。他们发现他们的奶奶——尼亚·坎亚达——在树荫里铺了一块垫子,正坐在上面休息。在当地的语言里,这个名字的意思是“坎亚达人民的女儿”。她是一个坚强美丽的女性。


ንያር ካንያዳ በክብር ወደቤቷ አስገባቻቸውና በደስታ መዝፈን ያዘች። የልጅ ልጆቿ ከከተማ የገዙላትን ስጦታዎች በደስታ ሰጧት። ‹‹መጀመሪያ የእኔን ስጦታ ክፈችው›› አለ ኦዶንጎ። ‹‹አይደለም፣ መጀመሪያ የኔን›› አለች አፒዮ።

尼亚·坎亚达欢迎他们来到自己的家里,和他们一起快乐地唱歌跳舞。他们的孙子也很高兴地把他们在城里买的礼物送给她。欧东格和阿皮尤吵着要奶奶先打开自己的礼物。


ስጦታዎችን ከከፈተች በኋላ አያትዬው የልጅ ልጆቿን መረቀቻቸው።

尼亚·坎亚达打开了礼物后,用传统的习俗祝福了她的孙儿们。


ከዚያም አዱኛና አፒዮ ወደ ውጪ ወጡ። ቢራቢሮዎችንና ወፎችን ማባረር ያዙ።

欧东格和阿皮尤跑出去玩儿了,他们追着蝴蝶和鸟儿,在它们后面跑。


ዛፍ ላይ ይወጣሉ፤ ሐይቁ ውስጥም ይንቦጫረቁ ነበር።

他们还爬树,跳进湖里,溅起了很多水花。


ሲመሽ ለራት ወደ ቤት መጡ። ምግባቸውን በወጉ ከመጨረሳቸው በፊት እንቅልፍ ጣላቸው።

天黑了,他们回到奶奶的家里吃晚饭,但他们太累了,还没吃完,就睡着了。


በሚቀጥለው ቀን አባታቸው ልጆቹን ከአያታቸው ጋር ትቷቸው ወደ ከተማ ተመለሰ።

第二天,爸爸开车回城了,把孩子们留给奶奶。


ኦዶንጎና አፒዮ አያታቸውን ቤት ውስጥ ስራ ያግዟቸው ነበር። ውሃ ይቀዳሉ፣ የማገዶ እንጨትም ይለቅማሉ። ዶሮዎች የጣሉትን እንቁላሎች ይሰበስባሉ፣ ቅጠላቅጠል ከአትክልት ስፍራው ይሰበስባሉ።

欧东格和阿皮尤帮助奶奶做家务。他们帮奶奶拎水,运柴。他们还帮奶奶从鸡窝里拿鸡蛋,在花园里摘蔬菜。


ንያር ካንያዳ የተለያዩ ምግብ አሰራሮችን ለልጆቹ አስተማረቻቸው። ሩዝና የተጠበሰ አሳ አሰራር እንዴት እንደሚሰራ አሳየቻቸው።

尼亚·坎亚达教他们煮乌咖喱,还教他们怎么做和烤鱼一起吃的椰子饭。


አንድ ቀን ጠዋት ኦዶንጎ የአያቱን ላሞች ሳር ለማጋጥ ወደመስክ ወሰዳቸው። ላሞቹም ወደጎረቤት ማሳ ሮጠው ገቡ። የማሳው ባለቤት ገበሬ በኦዶንጎ ተናደደበት። አስፈራራው፣ ሰብሉን ስለበሉበት ላሞቹን እንደሚወስድበት አስፈራራው። ከዚያ ቀን በኋላ ላሞቹ ዳግም ችግር እንዳይገጥማቸው ይጠነቀቅ ጀመር።

一天早上,欧东格帮奶奶去牧场上放牛,但是牛跑到了邻居的农场上,邻居很生气,威胁欧东格说,要没收了这些牛作为踩坏粮食的赔偿。从那天以后,欧东格很小心,不想再让这些牛惹麻烦了。


በሌላ ቀን ልጆቹ ከአያታቸው ጋር ወደገበያ ወጡ። የሚሸጥ ቅጠላቅጠል፣ ስኳርና ሳሙና ይዛለች። አብይ ለደንበኞቹ የሚሸጡ ነገሮችን ዋጋ ይናገራል። አፒዮ ደግሞ የተሸጡ እቃዎችን ለገዢዎች ትጠቀልልላቸዋለች።

有一天,孩子们和尼亚·坎亚达一起去集市上。奶奶有一个卖蔬菜、糖和肥皂的摊位。阿皮尤给顾客们报价钱,欧东格帮着顾客打包。


ሲጨርሱ ሁሉም በአንድ ላይ ሆነው ሻይ ጠጡ። አያታቸው ከሽያጭ ያገኘችውን ገንዘብ በመቁጠር አገዟት።

这天的工作结束后,他们坐在一起喝茶,帮奶奶数了数这天赚到的钱。


ብዙም ሳይቆዩ በዓላቱም አለፉ፤ ልጆቹም ወደ ከተማ መመለሻቸው ሆነ። ንያር ካንያዳ ለኦዶንጎ ኮፍያ፣ ለአፒዮ ደግሞ ሹራብ ሰጠቻቸው። ለመንገዳቸውም ስንቅ ቋጠረችላቸው።

很快,假期就结束了,孩子们要回城了。尼亚·坎亚达送给欧东格一顶帽子,送给阿皮尤一件毛衣。她帮孩子们装了点食物在路上吃。


አባታቸው ሊወስዳቸው ሲመጣ እነሱ በበኩላቸው መሄድ አልፈለጉም። ልጆቹ ንያር ካንያዳን አብራቸው ወደ ከተማ እንድትሄድ ጠየቀቻቸው። ፈገግ አለችና እንዲህ አለች፣ ‹‹አይ ልጆቼ ከተማ ለመኖር እንኳ አርጅቻለሁ። ዳግም ወደኔ ዘንድ እስክትመጡ እጠብቃችኋለሁ።››

当爸爸来接他们的时候,他们一点儿都不想走。孩子们求尼亚·坎亚达和他们一起去城里。她笑着说:“我太老了,不适合住在大城市里。我就在这个村子里面等你们,等你们下次再来。”


ኦዶንጎ እና አፒዮ ጥብቅ አድርገው አቀፏቸውና ተሰናበቷቸው።

欧东格和阿皮尤紧紧地抱着她,跟她告别。


ኦዶንጎ እና አፒዮ ወደ ትምህርት ቤት ሲመለሱ ለጓደኞቻቸው አገር ቤት ስለነበራቸው ቆይታ ነገሯቸው። አንዳንድ ልጆች የከተማ ህይወት ጥሩ እንደሆነ ያስባሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ገጠር የተሻለ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሁሉም ሰው ኦዶንጎ እና አፒዮ በጣም ግሩም የሆኑ አያት እንዳላቸው ይስማማሉ።

当欧东格和阿皮尤回到学校时,他们把村子里的生活告诉了伙伴们。一些人觉得城市生活很不错,另一些人觉得乡村生活更好。最重要的是,每个人都相信欧东格和阿皮尤的奶奶太棒啦!


作者: Violet Otieno
插图: Catherine Groenewald
译文: Dawit Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 4级
出处: 原文来自非洲故事书Holidays with grandmother
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 4.0 未本地化版本授权条款授权。
选项
返回故事列表 下载 PDF