በድሮ ዘመን አንድ ደስተኛ ቤተሰብ ነበረ።
Once upon a time,
there lived a happy
family.
አንድም ቀን እርስበርሳቸው ተጣልተው አያውቁም። ልጆቹም ቤተሰባቸውን ቤት ውስጥም ሆነ በመስክ ላይ ያግዙ ነበር።
They never fought with
each other. They helped
their parents at home
and in the fields.
ነገር ግን እሳት ወዳለበት አካባቢ እንዲጠጉ አልተፈቀደላቸውም።
But they were not
allowed to go near a
fire.
ስራቸውን ማከናወን የነበረባቸው በምሽት ነበር። ምክንያቱም የተሰሩት ከሰም ስለነበር!
They had to do all their
work during the night.
Because they were made of wax!
ነገር ግን ከልጆቹ አንደኛው በጠራራ ፀሐይ ለመውጣት ቋመጠ።
But one of the boys
longed to go out in the
sunlight.
አንድ ቀን ፍላጎቱ በጣም አየለ፤ ወንድሞቹም በጣም አስጠነቀቁት።
One day the longing
was too strong. His
brothers warned him…
ምን ያረጋል! ምክርም አልሰማ አለና፣ የፀሐዩ ሙቀትም አቀለጠው።
But it was too late!
He melted in the hot
sun.
ከሰም የተሰሩት ልጆችም በወንድማቸው ሁኔታ እጅግ አዘኑ።
The wax children were
so sad to see their
brother melting away.
ሆኖም እቅድ ነደፉ፤ የቀለጠውን ሰም አበጃጅተው እርግብ አደረጉት።
But they made a plan.
They shaped the lump
of melted wax into a
bird.
እርግቡን ወንድማቸውንም ትልቅ ተራራ ጫፍ ላይ አወጡት።
They took their bird
brother up to a high
mountain.
ፀሐይዋ ስትጠልቅ ርግቡ ጥዑም ዜማ እያዜመ በመብረር የጠዋት ጮራ እስክትወጣ ድረስ ጨረቃዋ ባደመቀችው ሌሊት ተንሸራሸረ።
And as the sun rose, he
flew away singing into
the morning light.