ቶም ለመብል የደረሱ ሙዞችን በቁና ተሸክሟል።
Tom carries a tray of ripe bananas.
ቶም ሙዞችን ለመሸጥ ወደ ገበያ ሄደ።
Tom goes to the market to sell bananas.
ሰዎች ገበያ ውስጥ ፍራፍሬ እየገዙ ነው።
People at the market are buying fruit.
ግን የቶምን ሙዝ የሚገዛው ጠፋ። ፍራፍሬ መግዛት የሚፈልጉት ከሴቶቹ ላይ ነበር።
But no one is buying
Tom’s bananas.
They prefer to buy fruit from women.
‹‹በኛ ማኅበረሰብ ውስጥ ፍራፍሬ የሚሸጡት ሴቶች ብቻ ናቸው›› ይላል ህዝቡ። ከዛም ‹‹ምን ዓይነት ሰው ነው ይሄ?›› ተባባሉ።
“In our community, only women sell fruit,” people say. “What kind of a man is this?” people ask.
ነገር ግን ቶም በፍጹም ተስፋ አልቆረጠም። ‹‹አለች ሙዝ፤ የኔን ጣፋጭ ሙዝ ግዙ!›› እያለ መለፈፍ ጀመረ።
But Tom does not give up.
He calls, “Buy my bananas!
Buy my sweet ripe bananas!”
አንዲት ሴትዮ አንድ ጉንጉን ሙዝ ከቁናው ላይ አነሳች። ከዛም በትኩረት ተመለከተችው።
One woman picks up a bunch of bananas from the tray.
She looks at the bananas carefully.
ሴትዮዋም ሙዙን ገዛች።
The woman buys the bananas.
ከዛ ሌሎች ሰዎችም መጡ። የቶምን ሙዞች እየገዙ መብላት ጀመሩ።
More people come to the stall.
They buy Tom’s bananas and eat them.
ወዲያው ቁናው ባዶ ሆነ። ቶምም ሸጦ ያገኘውን ገንዘብ ቆጠረ።
Soon, the tray is empty.
Tom counts the money he earned.
ከዚያም ቶም ሳሙና፣ ስኳርና ዳቦ ገዝቶ በቁናው ውስጥ አስቀመጠ።
Then Tom buys soap, sugar, and bread.
He puts the things in his tray.
ከዚያም የገዛውን ቁናው ውስጥ አድርጎ ወደቤቱ ሄደ።
Tom balances the tray on his head and goes home.