Back to stories list

ዶሮና ንስር Hen and Eagle

Written by Ann Nduku

Illustrated by Wiehan de Jager

Translated by Dawit Girma

Read by Abenezer Chane

Language Amharic

Level Level 3

Narrate full story

Reading speed

Autoplay story


በድሮ ጊዜ ዶሮና ንስር ጓደኛሞች ነበሩ። ከሌሎች የወፎች ዘር ጋርም በሰላም ይኖሩ ነበር። አንዳቸውም መብረር አይችሉም ነበር።

Once upon a time, Hen and Eagle were friends. They lived in peace with all the other birds. None of them could fly.


አንድ ወቅት፣ በምድር ሁሉ ላይ ረሃብ ተከሰተ። ንስር በጣም ራቅ ያለ ቦታ ሄዳ ምግብ መፈለግ ነበረባት። ከዚያም በጣም ደክሟት ተመለሰች። ‹‹ለመጓዝ በጣም ቀላል ዘዴ መኖር ነበረበት›› አለች ንስር።

One day, there was famine in the land. Eagle had to walk very far to find food. She came back very tired. “There must be an easier way to travel!” said Eagle.


ሌሊቱን ጣፋጭ እንቅልፍ ካሳለፈች በኋላ ዶሮ ግሩም ሃሳብ መጣላት። ከሌሎች ወፎች የወዳደቀ ላባ ሁሉ መልቀም ያዘች። ‹‹በሉ ከእኛ ላባ ላይ አነዚህን አብረን እናያይዛቸው›› አለች። ‹‹ምናልባት ይሄ ለመጓዝ ቀላል ያደርግልን ይሆናል››

After a good night’s sleep, Hen had a brilliant idea. She began collecting the fallen feathers from all their bird friends. “Let’s sew them together on top of our own feathers,” she said. “Perhaps that will make it easier to travel.”


ንስር በሰፈሩ መርፌ ያላት ብቸኛዋ ነበረች። ስለዚህ መጀመሪያ መስፋት ጀመረች። ለራሷ የሚያምር ጥንድ ክንፍ ሰራችና ከዶሮ በላይ መብረር ጀመረች። ዶሮ መርፌ ተዋሰች። ስትሰፋ ግን ወዲያውኑ ደከማት። መርፌውን መሳቢያ ውስጥ አስቀምጣ ለልጆቿ ምግብ ለማብሰል ወደ ማድቤት ገባች።

Eagle was the only one in the village with a needle, so she started sewing first. She made herself a pair of beautiful wings and flew high above Hen. Hen borrowed the needle but she soon got tired of sewing. She left the needle on the cupboard and went into the kitchen to prepare food for her children.


ሌሎቹ ወፎች ንስርን ርቃ ስትበር ተመልክተዋታል። ከዚያም ዶሮን ለራሳቸውም ክንፍ ለመስራት እንዲችሉ መርፌውን ታውሳቸው ዘንድ ጠየቋት። ወዲያው ወፎች በሰማዩ ላይ ከፍ ብለው ይበሩ ጀመር።

But the other birds had seen Eagle flying away. They asked Hen to lend them the needle to make wings for themselves too. Soon there were birds flying all over the sky.


የመጨረሻዋ ወፍ የተዋሰችውን መርፌ ስትመልስ ዶሮ በቦታው አልነበረችም። በመሆኑም ልጆቿ መርፌውን ይዘው ይጫወቱበት ጀመር። ተጫውተው ሲደክማቸው፣ መርፌውን አሸዋ ውስጥ ተውት።

When the last bird returned the borrowed needle, Hen was not there. So her children took the needle and started playing with it. When they got tired of the game, they left the needle in the sand.


ወደማታ ግድም ንስር ተመለሰች። በጉዞ ወቅት የላሉ አንዳንድ ላባዎችን ለመጠገን ፈልጋ መርፌውን ጠየቀች። ዶሮ መሳቢያው ስውጥ ተመለከተች፣ ማዕድ ቤት ፈለገች፣ በግቢው ውስጥም አየች። ነገር ግን መርፌው የትም መገኘት አልተቻለም።

Later that afternoon, Eagle returned. She asked for the needle to fix some feathers that had loosened on her journey. Hen looked on the cupboard. She looked in the kitchen. She looked in the yard. But the needle was nowhere to be found.


‹‹አንድ ቀን ብቻ ስጪኝ›› ብላ ዶሮ ንስርን ተለማመጠቻት። ‹‹ከዚያ ክንፍሽን ጠግነሽ ዳግም ምግብ ፍለጋ መብረር ትችያለሽ።›› ‹‹አንድ ተጨማሪ ቀን ብቻ›› አለች ንስር። ‹‹መርፌውን ማግኘት ባትችዪ ግን ከጫጩቶችሽ አንዷን እንደክፍያ ትሰጭኛለሽ።›› አለቻት።

“Just give me a day,” Hen begged Eagle. “Then you can fix your wing and fly away to get food again.” “Just one more day,” said Eagle. “If you can’t find the needle, you’ll have to give me one of your chicks as payment.”


ንስር በቀጣይ ቀን ስትመጣ ዶሮ አሸዋውን እየጫረች አገኘቻት፤ ግን መርፌ የሚባል የለም። ከዚያ ንስር ዝቅ ብላ በፍጥነት በመብረር ከዶሮዋ ጫጩቶች አንዷን ቀለበቻት። ይዛትም ርቃ በረረች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ ንስር ብቅ ባለች ቁጥር ዶሮ መርፌውን ፍለጋ አሸዋውን ስትጭር ታገኛታለች።

When Eagle came the next day, she found Hen scratching in the sand, but no needle. So Eagle flew down very fast and caught one of the chicks. She carried it away. Forever after that, whenever Eagle appears, she finds Hen scratching in the sand for the needle.


የንስር ክንፍ ጥላ መሬቱ ላይ ባረፈ ጊዜ ዶሮ ጫጩቶቿን ታስጠነቅቃለች። ‹‹ግልጽ ቦታ ላይ አትሁኑ፣ ጥፉ አምልጡ!›› ጫጩቶቹም እንዲህ ይላሉ፦ ‹‹ሞኞች አይደለንም፣ እንሮጣለን።››

As the shadow of Eagle’s wing falls on the ground, Hen warns her chicks. “Get out of the bare and dry land.” And they respond: “We are not fools. We will run.”


Written by: Ann Nduku
Illustrated by: Wiehan de Jager
Translated by: Dawit Girma
Read by: Abenezer Chane
Language: Amharic
Level: Level 3
Source: Hen and Eagle from African Storybook
Creative Commons License
This work is licensed under a Creative Commons Attribution 3.0 International License.
Options
Back to stories list Download PDF