ይቺ ካላይ ነች። ዕድሜዋ 7 ዓመት ነው። የስሟ ትርጉም በቋንቋዋ በሉቡኩሱ ‹‹ጥሩዋ ልጅ›› ማለት ነው።
This is Khalai.
She is seven years old.
Her name means ‘the
good one’ in her
language, Lubukusu.
ካላይ ከእንቅልፏ ስትነሣ ከአንድ የብርቱካን ዛፍ ጋር ትነጋገራለች። ‹‹እባክህ አንተ የብርቱካን ዛፍ ትልቅ ሁንና ብዙ የበሳሰሉ ብርቱካኖችን ስጠን›› ትለዋለች።
Khalai wakes up and
talks to the orange tree.
“Please orange tree,
grow big and give us
lots of ripe oranges.”
ካላይ ወደ ትምህርት ቤት ትሄዳለች። በመንገዷም ላይ ከሳሩ ጋር ታወራለች። ‹‹እባክህ ሳር አረንጓዴነትህን ግፋበት እንጂ እንዳትደርቅ።››
Khalai walks to school.
On the way she talks to
the grass. “Please
grass, grow greener
and don’t dry up.”
ካላይ የዱር አበቦችን አልፋ ሄደች። ‹‹እባካችሁ አበቦች ለጌጥ ጸጉሬ ላይ እንዳረጋችሁ ማበባችሁን ቀጥሉ።››
Khalai passes wild
flowers. “Please
flowers, keep blooming
so I can put you in my
hair.”
በትምህርት ቤት ግቢ ካለው ዛፍ ጋርም ካላይ ትነጋገራለች። ‹‹እባክህ አንተ ዛፍ ከጥላው ስር ቁጭ ብለን እንድናነብ ትላልቅ ቅርንጫፎችን አብቅልልን።››
At school, Khalai talks
to the tree in the
middle of the
compound. “Please
tree, put out big
branches so we can
read under your shade.”
ካላይ በትምህርት ቤቷ ዙሪያ ካለው ቁጥቋጦም ጋር ታወራለች። ‹‹ጠንካራ ሆናችሁ እደጉ፤ መጥፎ ሰዎች እንዳያልፉ አግዷቸው።››
Khalai talks to the
hedge around her school.
“Please grow strong
and stop bad people
from coming in.”
ካላይ ከትምህርት ቤት ወደ ቤቷ ስትመለስ የብርቱካኑን ዛፍ አየችው። ‹‹የብርቱካን ፍሬዎችህ ገና አልበሰሉም?›› ስትል ካላይ ጠየቀችው።
When Khalai returns
home from school, she
visits the orange tree.
“Are your oranges ripe
yet?” asks Khalai.
‹‹የብርቱካኑ ፍሬዎች ገና አልበሰሉም›› ካላይ አለች። ‹‹ነገ እመለስና አይሃለሁ የብርቱካን ዛፍ›› አለች ካላይ። ‹‹ምናልባት ያኔ የበሰሉ የብርቱካን ፍሬዎች አዘጋጅተህ ትጠብቀኝ ይሆናል!››
“The oranges are still
green,” sighs Khalai.
“I will see you tomorrow
orange tree,” says
Khalai. “Perhaps then
you will have a ripe
orange for me!”