下载 PDF
返回故事列表

ከቀየዬ ወጥቼ ከተማ ስገባ 离家进城的那一天

作者 Lesley Koyi, Ursula Nafula

插图 Brian Wambi

译文 Dawit Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 3级

将整故事念出来 本故事尚未有语音版。


በመንደራችን ያለው መናሓሪያ በሰዎች እና በታጨቁ አውቶብሶች ተጨናንቆ ነበር። መሬት ላይ ሊጫኑ የተዘጋጁ በርካታ ቁሳቁስ ነበሩ። ረዳቶች አውቶብቸው የሚሄድበትን ቦታ በጩኅት ይጣሩ ነበር።

在我生活的村庄里,有一个小小的大巴车站。大巴车站虽然小,但是人来车往,非常热闹,地上常常堆满了装载的货物,售票员叫喊着大巴车开往的方向。


‹‹ከተማ! ከተማ! ልንወጣ ነው፤ የሞላ!›› እያለ ወያላው ሲጮህ ሰማሁ። አዎ ልሳፈርበት የምፈልገው አውቶብስ ይሄ ነበር።

我听到售票员喊“进城啦!进城啦!往西去!”这就是我要乘坐的大巴车。


የከተማ አውቶብሱ እየሞላ ነው፤ ነገር ግን አሁንም ሌሎች ሰዎች ለመግባት ይጋፋሉ። የተወሰኑት እቃቸውን አውቶብሱ ኪስ ውስጥ ይጭናሉ። ሌሎቹ ደግሞ በአውቶብሱ ውስጥ።

进城的大巴车几乎坐满了,但是人们还是不停地往里面挤。一些人把行李放在车顶,还有一些人把行李放在车厢里的架子上。


አዲስ ገቢ መንገደኞች ትኬታቸውን ቶሎ ቶሎ አየት እያደረጉ አውቶብሱ ውስጥ መቀመጫ ቦታ መኖሩን ያያሉ። ህጻኖቻቸውን ያቀፉ ሴቶች ለረጅሙ መንገድ ተመቻችተው ተቀምጠዋል።

刚上车的乘客们紧紧地抓着他们的车票,在拥挤的车厢里寻找座位,带着小孩的妇女们都坐得舒舒服服的。


በመስኮቱ አጠገብ ጥብቆ ገብቼ ተቀመጥኩ። ከኔ አጠገብ የተቀመጠው ሰው አረንጓዴ የላስቲክ ሻንጣ ይዟል። አሮጌ ነጠላ ጫማ ተጫምቷል፤ ልባሽ ኮት ለብሷል፤ የተበሳጨም ይመስላል።

我挤到了窗边的一个座位里。旁边的乘客紧紧地抓着一个绿色的塑料包裹。他穿着破旧的凉鞋和外套,看起来很紧张。


በመስኮቱ አሻግሬ እየተመለከትኩ ወዲያው ያደኩበትን መንደሬን እየለቀኩ መሆኑን አስተዋልኩ። ወደ ግዙፍ ከተማ እየተጓዝኩ ነበር።

我朝窗外看去,这才意识到,我正在离开我长大的村庄,我要进城了!


መኪናው ሞልቷል፤ ሁሉም መንገደኞች ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል። ሻጮች አሁንም እየተጋፉ ሸቀጦቻቸውን ለመንገደኞች ለመሸጥ ወደ አውቶብሱ ይገባሉ። ሁሉም ሰው የሚገዛው ነገር ፍለጋ ይሄን ስጠኝ ያን ስጠኝ እያለ ይጯጯህ ጀመር። የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ግን እኔን ያዝናናኝ ይዟል።

货物都装载完了,乘客们都坐好了。小商贩们还在努力地挤到车厢里,向乘客们大声叫卖着货物。他们的话听起来怪好笑的。


ጥቂቶቹ ተጓዦች የሚጠጣ ነገር ገዙ፣ ሌሎቹ ደግሞ የሚበላ ነገር ገዝተው ይበሉ ጀመር። እንደኔ ምንም ገንዘብ የሌለን ደግሞ ዝም ብለን እንመለከታለን።

有一些乘客买了饮料,还有一些乘客买了零食,正准备拆开来吃。像我一样没有钱的人只能看着。


ይህ ሁሉ ድርጊት አውቶብሱ የመነሳት ጩኸት ሲያሰማ ረገብ ይላል፤ ሻጮችም ለመውጣት እየተጣደፉ እግረ መንገዳቸውን ፈጠን ፈጠን እያሉ እየተጯጯሁ ይሸጣሉ።

大巴车滴滴叫了两声,要开了,小商贩的活动戛然而止。售票员喊着,赶他们下车。


ሻጮቹ ለመውጣት እርስበራሳቸው ይጋፋሉ። አንዳንዶቹ መንገደኞቹን ‹‹አንዴ ልለፍ›› እያሉ ሲወጡ ሌሎቹ ደግሞ ለመሸጥ የመጨረሻ ሙከራ ያደርጋሉ።

小商贩们推推搡搡下了车。一些人还在忙着找零钱,还有一些人赖着想最后再做点生意。


አውቶብሱ ሲነሳ እኔ በመስኮት በኩል ወደ አፈጠጥኩ። እንደው ወደቀየዬ ዳግም እመለስ ይሆን እያልኩ ተደነቅሁ።

大巴车缓缓离开了车站,我看着窗外,不知道今后会不会有机会回来了。


መንገድ ላይ እየተጓዝን የአውቶብሱ ውስጥ በጣም ይሞቃል። ለመተኛት አስቤ አይኔን ጨፈንኩ።

旅程渐渐展开,车厢里慢慢热了起来,我闭上眼睛,想小睡一会儿。


ሃሳቤ ሁሉ ግን ወደቤቴ ነበር። እንደው እናቴ ደህና ትሆን ይሆን? እንደው ጥንቸሎቼስ ገንዘብ ያወጡ ይሆን? ወንድሜስ አስታውሶ ችግኞቼን ውሃ ያጠጣ ይሆን?

但我的思绪却飞回了家。我的妈妈安全吗?我的兔子会卖了赚钱吗?我的弟弟会帮着给小树苗浇水吗?


በመንገዴም አጎቴ በዛ ትልቅ ከተማ የሚኖርበትን ቦታ ስም አስታወስኩ። ሳንቀላፋ ሁሉ ይሄን ስም አነበንባለሁ።

在路上,我努力记住我叔叔在城市里的地址。我迷迷糊糊地说着地址,沉沉地睡去。


ከዘጠኝ ሰዓታት በኋላ ወያላ ወደመጣሁበት መንደር ተመላሽ የሚጓዝ ሰው እየጮኸ ሲጣራ ነቃሁ። ትንሽ ቦርሳዬን ይዤ ከአውቶብስ ወረድኩ።

过了九个小时,我被售票员的叫喊声吵醒了,他在喊乘客坐车回村庄。我一把抓住我的包,跳下了车。


ተመላሹ አውቶብስ በፍጥነት እየሞላ ነው። ወዲያው ፊቱን ወደምስራቅ አዙሮ መመለስ ጀመረ። አሁን ለኔ እጅግ አስፈላጊው ነገር አጎቴ የሚኖርበትን ሰፈር ማፈላለግ መጀመር ነው።

回程的大巴车很快就坐满了,不久就要开回东边的村庄去了。对我来说,现在最重要的事情就是找到我叔叔的家。


作者: Lesley Koyi, Ursula Nafula
插图: Brian Wambi
译文: Dawit Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 3级
出处: 原文来自非洲故事书The day I left home for the city
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 4.0 未本地化版本授权条款授权。
选项
返回故事列表 下载 PDF