下载 PDF
返回故事列表

የሳኪማ መዝሙር 萨可满的歌声

作者 Ursula Nafula

插图 Peris Wachuka

译文 Dawit Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 3级

将整故事念出来

播放速度

自动念故事


ሳኪማ ከቤተሰቦቹና ከ4 ዓመት ታላቅ እህቱ ጋር ይኖራል። የሚኖሩት ባንድ ሃብታም ሰውዬ መሬት ላይ ነው። ባለሳር ክዳን ጎጇቸው በመደዳ ከበቀሉ ዛፎች ማዶ ትገኛለች።

萨可满和他的父母,还有四岁的妹妹住在一起,他们住在一个富人的土地上,他们的茅草屋在一排大树的后面。


ሳኪማ 3 ዓመት ሲሆነው ታመመና የዓይን ብርሃኑን አጣ። ሳኪማ ባለተሰጥኦ ልጅ ነበር።

萨可满三岁的时候,生了一场大病,从此,萨可满就看不见了,其实萨可满是一个非常有天赋的孩子。


ሳኪማ የ6 ዓመት ልጆች እንኳ የማይሰሯቸውን በርካታ ነገሮችን ማድረግ ይችላል። ለምሳሌ ከመንደሩ ትልልቅ ሴቶች ጋ ቁጭ ብሎ ጠቃሚ ቁምነገሮችን ይወያያል።

萨可满今年六岁,他会做很多同龄的男孩不会做的事情,比如,萨可满能和村里的老人坐在一起讨论重要的事情。


የሳኪማ ቤተሰቦች በሃብታሙ ሰው ቤት ውስጥ ይሰራሉ። ጠዋት በማለዳ ከቤታቸው ይወጡና ማታ ወደቤታቸው ይመለሳሉ። ሳኪማ ደግሞ ከትንሽ እህቱ ጋር ይቆያል።

萨可满的父母在富人的家里工作。他们每天早出晚归,萨可满就和妹妹呆在家里。


ሳኪማ መዝሙር መዘመር ይወዳል። አንድ ቀን እናቱ ጠየቀችው፣ ‹‹ከየት ነው እነዚህን መዝሙሮች የተማርካቸው ሳኪማ?››

萨可满很喜欢唱歌。有一天,他的妈妈问他:“萨可满,你从哪儿学了这些歌?”


ሳኪማም መለሰ ‹‹ራሳቸው ይመጣሉ እማዬ። በጭንቅላቴ እሰማቸዋለሁ ከዚያም እዘምራለሁ።››

萨可满回答说:“它们就这样出现在我的脑海里,我想到了这些歌,就把它们唱了出来。”


ሳኪማ ለእህቱ ይዘምርላታል በተለይ ሲርባት ሲርባት። ተወዳጅ ዜማዎቹን ሲያዜም እህቱ ትሰማዋለች። ወዲያ ወዲህ እየተወዛወዘች በዜማው ትመሰጣለች።

萨可满很喜欢给他的妹妹唱歌,特别是她肚子饿的时候。妹妹听着萨可满唱他最喜欢的歌,跟着甜美的歌声摆动起来。


‹‹ደግመህ ደጋግመህ ልታዜምልኝ ትችላለህ ሳኪማ›› እህቱ ለመነችው። ሳኪማም ጥያቄዋን ተቀብሎ እስኪበቃት ደጋግሞ አዜመላት።

萨可满的妹妹经常求他:“再唱一次吧!”萨可满唱了一遍又一遍。


አንድ ምሽት ቤተሰቦቹ ወደቤት ሲመለሱ በጣም ተክዘው ነበር። ሳኪማ የሆነ ነገር እንደተፈጠረ አወቀ።

有一天晚上,萨可满的父母回到家以后一句话也不说。萨可满知道一定发生了什么不好的事情。


‹‹እማዬ፣ አባዬ ምንድነው? ምን ችግር አለ?›› ሳኪማ ጠየቀ። የሃብታሙ ሰው ልጅ መጥፋቱን ሳኪማ ተረዳ። ሰውዬው በጣም አዘነ፣ ብቸኝነትም ተሰማው።

萨可满问爸爸妈妈发生了什么事,他这才知道,原来富人的儿子失踪了,富人孤单一人,很伤心。


‹‹አዜምለታለሁ። እንደገናም ደስተኛ ይሆናል›› አለ ሳኪማ ለቤተሰቦቹ። ቤተሰቦቹ ግን ጀሮ ዳባ ልበስ አሉት። ‹‹እሱ በጣም ሃብታም ነው። አንተ ደግሞ ተራ አይነ ስውር ነህ። የአንተ ዜማ የሚረዳው ይመስልሃል?››

萨可满对父母说:“我可以给他唱歌,这样他就会高兴起来了。”但是萨可满的父母不喜欢这个主意:“他很有钱,而你只是一个看不见的小男孩。你以为你的歌声会帮到他吗?”


ነገር ግን፣ ሳኪማ ተስፋ አልቆረጠም። ትንሷ እህቱም ትረዳዋለች። ‹‹የሳኪማ ዜማዎች በራበኝ ጊዜ ያረጋጉኛል። ሃብታሙን ሰውዬም እንዲሁ ያረጋጉታል።››

但是萨可满没有放弃,他的妹妹也鼓励他。她说:“萨可满的歌声能赶走饥饿,他肯定也能安慰富人。”


በቀጣዩ ቀን ወደ ሃብታሙ ቤት መርታ እንድትወስደው ሳኪማ እህቱን ጠየቃት።

第二天,萨可满让他的妹妹带他去富人的房子。


ከአንድ ትልቅ መስኮት በታች ቆሞ ተወዳጁን ዜማ አዜመ። ቀስ ብሎ የሃብታሙ ሰው ጭንቅላት በትልቁ መስኮት በኩል መታየት ጀመረ።

他站在一扇大窗户的下面,开始唱他最喜欢的歌。慢慢的,富人的脑袋从窗户里伸出来。


ሰራተኞቹ እየሰሩ የነበረውን አቆሙ። የሳኪማን ቆንጅዬ ዜማ ማዳመጥ ጀመሩ። ነገር ግን አንድ ሰው እንዲህ አለ ‹‹ማንም ሰው ቢሆን አለቃችንን ሊያዝናናው ወይም ሊያጽናናው የሚችል የለም። ይሄ አይነ ስውር ልጅ የሚችል ይመስለዋል እንዴ?››

工人们停下了工作。他们仔细地听着萨可满唱歌。有一个人说:“从来没有人能安慰老板,这个看不见的男孩觉得他可以做到吗?”


ሳኪማ ማዜሙን ጨረሰና ሊመለስ ሲል ሃብታሙ ሰውዬ ፈጥኖ ወጣና ‹‹እባክህ እንደገና አዚም›› አለው።

萨可满唱完了,准备离开。富人跑出来,说:“请再唱一遍吧!”


በዚያው ቅጽበት ሁለት ሰዎች በቃሬዛ አንድ ሰው ይዘው መጡ። የሃብታሙን ሰውዬ ልጅ ተነክሶ ጉዳት ደርሶበት መንገድ ዳር ወድቆ ነው ያገኙት።

就在那时,两个人抬着担架走来了,担架上是富人的儿子!他们发现这个人被打得面目全非,躺在路边。


ልጁን ደግሞ ስላየው ሃብታሙ ሰውዬ በጣም ተደሰተ። ምቾት ስለሰጠው ሳኪማ ተደሰተ። ከዚያ ልጁንና ሳኪማን ወደ ሃኪም ቤት ወሰዳቸው፤ ሳኪማም እንደገና አይኑ ማዬት ቻለ።

富人很高兴儿子找回来了。为了感谢萨可满安慰他,他把萨可满和他的儿子一起送到了医院,萨可满很快就会恢复视力了。


作者: Ursula Nafula
插图: Peris Wachuka
译文: Dawit Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 3级
出处: 原文来自非洲故事书Sakima's song
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 4.0 未本地化版本授权条款授权。
选项
返回故事列表 下载 PDF