下载 PDF
返回故事列表

የአያቴ ሙዞች 奶奶的香蕉

作者 Ursula Nafula

插图 Catherine Groenewald

译文 Dawit Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 4级

将整故事念出来

播放速度

自动念故事


የአያቴ የአትክልት ስፍራ ግሩም ነው፤ ጥራጥሬው፣ ገብሱ፣ ካዛቫው በሽበሽ ነው። ከሁሉም ሙዙ ይበልጣል። ምንም እንኳ አያቴ በርከታ የልጅ ልጆች ቢኖራትም እኔን አብልጣ እንደምትወደኝ በምስጢር አውቃለሁ። ደብቃኛለች- ሙዞችን የት እንደምታመርት። ሁልጊዜ ነው ወደቤቷ የምትጋብዘኝ። አንዳንድ ምስጢሮችንም ታወራኛለች። አንድ ምስጢር ብቻ ግን አልነገረችኝም ነበር። እሱም ሙዞቹን የት እንዲበስሉ እንዳረገች ነበር።

奶奶有一座美丽的大花园,里面种满了高粱,杂谷和木薯,但里面最棒的是香蕉。奶奶虽然有很多孙子孙女,但我心里知道她最喜欢我。她常常邀请我去她家,告诉我一些小秘密。但是有一个秘密,她从来没有告诉我,那就是她催熟香蕉的办法。


አንድ ቀን አንድ ትልቅ ቅርጫት ከአያቴ ቤት ውጭ ጸሐይ ላይ ተሰጥቶ ተመለከትኩ። ምን ይሆን ብዬ ሳሰላስል ‹‹ያ ምትሃተኛ ቅርጫቴ›› ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ። ከቅርጫቱ ጎን ብዙ የሙዝ ቅጠሎች ይታያሉ። በጣም በመጓጓት ‹‹አያቴ የምን ቅጠሎች ናቸው›› ብዬ ጠየኳት። ያገኘሁት ብቸኛ ምላሽም ‹‹ምትሃተኛ ቅጠሎቼ ናቸው›› የሚል ነበር።

有一天,我看到奶奶在门外放了一个巨大的麦秆编成的篮子。我问奶奶这是做什么的,奶奶却只说:“这是我的神秘篮子。”篮子旁边放了几片香蕉叶子,奶奶把叶子来回翻动。我很好奇,问奶奶:“这些叶子是做什么的?”奶奶却只说:“这是我的神秘叶子。”


አያቴን፣ ሙዞቹን፣ የሙዝ ቅጠሎችንና ትልቁን ቅርጫት መመልከት በጣም አስደሳች ነበር። ነገር ግን አያቴ የሆነ ነገር እንዳመጣ ወደ እናቴ ዘንድ ላከችኝ። ‹‹እባክሽ አያቴ፣ ስትሰሪ ልይ…›› ‹‹አንቺ ልጅ፣ ድርቅ አትበዪ፣ ዝም ብለሽ የተባልሽውን አድርጊ›› አለች። ወዲያው እየሮጥኩ ሄድኩ።

我好奇地看着奶奶,香蕉,香蕉叶子还有那个巨大的麦秆编成的篮子。但奶奶却把我打发到妈妈那儿跑腿。我求奶奶:“让我留下来看一看吧!”奶奶却坚持说:“别固执了,按我说的去做。”我只好跑开了。


ስመለስ አያቴ ውጭ ተቀምጣ አገኘኋት፣ ነገር ግን ቅርጫቱም ሆነ ሙዞቹ አልነበሩም። ‹‹አያቴ፣ የታለ ቅርጫቱ፣ የታሉ ሙዞቹ ሁሉ፣ እና የታለ…›› ግን ያገኘሁት ብቸኛ ምላሽ ‹‹ከምትሃተኛው ቦታዬ ጋር ነው ያሉት›› የሚል ነበር። በጣም ነው ያስከፋኝ።

当我回来的时候,奶奶正坐在外面休息,但是篮子和香蕉都不见了!我问奶奶:“篮子去哪儿了?香蕉去哪儿了?还有那些……”奶奶却说:“它们都在一个神秘的地方。”我太沮丧了!


ከሁለት ቀናት በኋላ አያቴ ምርኩዟን እንዳመጣላት ወደመኝታ ቤቷ ላከችኝ። በሩን እንደከፈትኩት ወዲያውኑ ደስ የሚል አዲስ የሙዝ መዓዛ አወደኝ። ከውስጥ ደግሞ የአያቴ ምትሃተኛ ቅርጫት ነበረች። በአሮጌ ብርድልብስ በደንብ ተደብቃለች። ብድግ አረኩና ያን የሚያውድ መዓዛ በደንብ አሸተትኩት።

过了两天,奶奶让我从她的卧室拿拐杖给她。我一打开门,就闻到了熟香蕉的味道。原来奶奶的神秘篮子就放在卧室里!它上面盖了一条旧毯子,我掀起毯子,使劲地闻着那香味。


የአያቴ ድምጽ ከተመስጦዬ አነቃኝ። ‹‹ምን እያረሽ ነው? ቶሎ በይና ምርኩዜን አምጪልኝ››። ምርኩዟን ይዤ ቶሎ ሄድኩ። ‹‹ለምንድን ነው የምትስቂው?›› አያቴ ጠየቀችኝ። ከምትሃተኛ ቦታዋ ላይ ያለውን ድንቅ መዓዛ አሁንም ድረስ እያጣጣምኩ እንዳለሁ ጥያቄዋ አስታወሰኝ።

奶奶喊我的时候,我吓了一跳:“你在做什么?快把我的拐杖拿来。”我赶紧把拐杖拿出去给奶奶。奶奶看着我,问:“你在笑什么?”我这才意识到,我还在因为发现了这个神奇的秘密窃笑着。


በሚቀጥለው ቀን አያቴ እናቴን ለመጠየቅ ስትመጣ እኔ የሙዞችን ሁኔታ ለመጨረሻ ጊዜ ለማጣራት ወደአያቴ ቤት በፍጥነት ሄድኩ። በጣም የደረሱ የሚያምሩ ሙዞች አገኘሁ። አንድ ወሰድኩና በልብሴ ደበኩ። ቅርጫቱን መልሼ ሸፈንኩና ከቤቱ ጀርባ ሄጄ ቶሎ በላሁት። በጣም ጣፋጭ ሙዝ ነበር፣ እንደዛ የሚጣፍጥ በልቼ አላውቅም።

第二天,奶奶来看我妈妈,我又跑到奶奶家去偷看那些熟香蕉。有一把香蕉已经非常熟了。我采了一根香蕉,把它藏在我的裙子里。我小心地盖好篮子,跑到房子后面,偷偷地把香蕉吃了:这是我吃过的最美味的香蕉!


በቀጣይ ቀን አያቴ አትክልት ስፍራው ውስጥ ቅጠላቅጠል እየቀነጠሰች እያለ ቀስ ብዬ ተደብቄ ወደሙዞቹ ሄድኩ። ሁሉም ለመብል ዝግጁ የሆኑ ናቸው። በአንድ የተያያዘ አራት ሙዞችን መውሰድ አልፈለኩም። ወደ በሩ በተረከዜ ቀስ እያልኩ ስራመድ አያቴ ስትስል ሰማኋት። ሙዞቹን በልብሶቼ ውስጥ ደበኩና ከበስተኋላዋ መራመድ ጀመርኩ።

第二天,我趁奶奶在花园里摘蔬菜的时候,偷偷跑进房间,去看那些香蕉,香蕉差不多全都熟了。我禁不住诱惑,拿了四根香蕉。我踮起脚离开房间,听到奶奶在咳嗽。我把香蕉藏在裙子下面,若无其事地走开了。


ቀጣዩ ቀን የገበያ ቀን ነበር። አያቴ በጠዋት ነቅታለች። እሷ ሁልጊዜ የደረሱ ሙዞችንና ካዛቫዎችን ለመሸጥ ገበያ ትወስዳለች። በዛ ቀን ልጎበኛት ቶሎ አልሄድኩም፤ ሆኖም ከርሷ ለመራቅም አልቻልኩም።

第二天是奶奶赶集的日子。奶奶很早就醒来了,她把成熟的香蕉和木薯运到集市上去卖。我那天没有急着去看她,但我知道,我不可能永远躲着奶奶。


ወደምሽት ላይ እናቴ፣ አባቴና አያቴ ጠሩኝ። ለምን እንደሆነ አወኩ። ማታ ስተኛ ከአያቴ፣ ከቤተሰቤም ሆነ ከሌላ ከማንም ሰው ላይ መስረቅ እንደሌለብኝ ለራሴ ቃል ገባሁ።

那天傍晚,我被爸爸、妈妈和奶奶叫过去。我知道他们为什么找我。那天晚上,当我上床睡觉的时候,我知道我再也不会偷东西了,不偷奶奶的,不偷爸妈的,不从任何人那里偷东西。


作者: Ursula Nafula
插图: Catherine Groenewald
译文: Dawit Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 4级
出处: 原文来自非洲故事书Grandma's bananas
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 3.0 未本地化版本授权条款授权。
选项
返回故事列表 下载 PDF