下载 PDF
返回故事列表

ኖዚቤሌና ሦስቱ ጸጉሮች 诺孜贝儿和三根头发

作者 Tessa Welch

插图 Wiehan de Jager

译文 Mezemir Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 3级

将整故事念出来

播放速度

自动念故事


በድሮ ጊዜ ሦስት ሴቶች እንጨት ለመሰብሰብ ከቤታቸው ወጥተው ነበር።

很久很久以前,有三个女孩,她们一起外出找柴火。


ሞቃት ቀን ስለነበር ለመዋኘት ወደ ወንዝ ወረዱ። ተጫወቱ፤ ውኃ ተራጩ፤ ዋኙ።

天很热,她们跳下河游了个泳。她们一边游泳,一边嬉戏,溅出很多水花。


ድንገት ምሽት መሆኑን ተገነዘቡ። ወደ መንደራቸውም ተጣደፉ።

突然,她们意识到天已经很晚了,匆匆忙忙赶回村子。


እቤታቸው ሊደርሱ ሲሉ ኖዚቤሌ እጇን አንገቷ ላይ አደረገች። የአንገት ጌጧን ረስታዋለች! ‹‹እባካችሁ አብራችሁኝ ተመለሱ!›› ብላ ባልንጀሮቿን ለመነቻቸው። ጓደኞቿ ግን በጣም እንደዘግየች ነገሯት።

当她们快到家的时候,诺孜贝儿摸了摸她的脖子:她把项链落在了外面。于是她请求她的朋友们:“和我一起回去找找吧!”但她的朋友们都说太晚了。


ስለዚህ ኖዚቤሌ ወደ ወንዙ ብቻዋን ተመለሰች። የአንገት ጌጧንም አግኝታ ወደ ቤቷ ለመመለስ ተቻኮለች፤ ነገር ግን በጨለማ ውስጥ ጠፋች።

诺孜贝儿一个人回到河边,一找到了项链,就赶忙回家,但天太黑了,她迷路了。


ከሩቅ ከአንዲት ጎጆ የሚወጣ ብርሃን አየች። ወደሱም ሄዳ በሩን አንኳኳች።

她远远地看见有个小木屋,木屋里有一丝光亮。她跑到木屋门口,敲了敲门。


ባልተጠበቀ ሁኔታ ዉሻ በሩን ከፈተላት። ‹‹ምን ፈልገሽ ነው?›› አላት። ‹‹ጠፍቻለሁ፤ እና ማደሪያ ቦታ ፈልጌ ነበር›› ብላ ነገረችው። ‹‹ነይ ግቢ፤ አለዚያ እነክስሻለሁ!›› አላት ዉሻው። ስለዚህ ኖዚቤሌ ገባች።

诺孜贝儿吃了一惊,开门的是一只会说话的狗:“你来干嘛?”诺孜贝儿说:“我迷路了,我要找个地方睡觉。”狗回答说:“进来吧,不然我就咬你!”然后诺孜贝儿就进了屋。


ከዚያም ዉሻው ‹‹ምግብ አብስዪልኝ!›› አላት። ‹‹እንዴ፣ እኔ እኮ ለዉሻ ምግብ ሰርቼ አላውቅም›› ብላ መለሰችለት። ‹‹ስሪልኝ፤ አለዚያ እነክስሻለሁ!›› አላት ዉሻው። ስለዚህ ኖዚቤሌ ለዉሻው ምግብ ሰራችለት።

狗说:“给我做饭!”诺孜贝儿回答说:“但我从来没有给狗做过饭。”狗说:“快做饭,不然我就咬你。”诺孜贝儿没办法,只能给狗做了一些吃的。


ከዚያም ዉሻው ‹‹አልጋዬን አንጥፊልኝ!›› አላት። ኖዚቤሌም ‹‹እኔ እኮ ለዉሻ አልጋ አንጥፌ አላውቅም›› ብላ መለሰችለት። ‹‹አንጥፊልኝ፤ ያለዚያ እነክስሻለሁ!›› አላት ዉሻው። ስለዚህ ኖዚቤሌ አነጠፈችለት።

狗说:“给我铺床!”诺孜贝儿回答说:“但我从来没有给狗铺过床。”狗说:“快铺床,不然我就咬你。”诺孜贝儿没办法,只能给狗铺了床。


በየቀኑ ለዉሻው ምግብ መስራት፣ ማጽዳትና ማጠብ ስራዋ ሆነ። ከዚያም አንድ ቀን ዉሻው ‹‹ኖዚቤሌ፣ ዛሬ ጓደኞቼን ልጠይቅ እሄዳለሁ። እኔ ከመምጣቴ በፊት ቤቱን አጽጂ፤ ምግብ ስሪ፤ የሚተጣጠቡትንም ነገሮች እጠቢ›› አላት።

诺孜贝儿每天都要给狗做饭,打扫屋子,洗衣服。有一天,狗说:“诺孜贝儿,我今天要出门见朋友。在我回来之前,你要打扫好屋子,做好饭,洗好衣服。”


ዉሻው እንደሄደ ኖዚቤሌ ከራሷ ላይ ሦስት ጸጉሮችን ከጭንቅላቷ ላይ ነቀለች። አንዱን ጸጉር ከአልጋው ስር፣ አንዱን ከበሩ ኋላ፣ እና ሌላውን ደግሞ በከብቶቹ በረት አስቀመጠቻቸው።

狗一走,诺孜贝儿就从头上拔了三根头发下来。她把一根头发放在床下,一根放在门背后,还有一根放在篱笆上。然后诺孜贝儿用尽全力跑回了家。


ዉሻዉም እንደተመለሰ ኖዚቤሌን ፈለጋት። ‹‹ኖዚቤሌ፣ የት ነሽ?›› ብሎ ተጣራ። ‹‹አልጋው ስር ነኝ›› አለ የመጀመሪያው ጸጉር። ‹‹በሩ ጀርባ ነኝ›› አለ ሁለተኛው ጸጉር። ‹‹በረት ውስጥ ነኝ፣›› አለ ሌላኛው ጸጉር።

当狗回到家的时候,它开始找诺孜贝儿:“诺孜贝儿,你在哪里?”第一根头发说:“我在这儿,在床底下。”第二根头发说:“我在这儿,在门背后。”第三根头发说:“我在这儿,在篱笆上。”


ከዚያም ዉሻው ኖዚቤሌ እንዳታለለችው ገባው። ስለዚህ ወደ መንደሩ እየተሯተሯጠ ፈለጋት። የኖዚቤሌ ወንድሞች ግን ትላልቅ ዱላዎች ይዘው እየጠበቁት ነበር። ውሻው ተመልሶ ሮጠ፤ ከዚያም በኋላ በመንደሩ በጭራሽ ታይቶ አያውቅም።

狗明白了诺孜贝儿耍的花招。它一路跑到诺孜贝儿的村庄,但是诺孜贝儿的兄弟们正拿着棍子等着它呢!狗见状不妙,赶紧跑开了,从此再也没人见过它。


作者: Tessa Welch
插图: Wiehan de Jager
译文: Mezemir Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 3级
出处: 原文来自非洲故事书Nozibele and the three hairs
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 3.0 未本地化版本授权条款授权。
选项
返回故事列表 下载 PDF