下载 PDF
返回故事列表

ማጎዝዌ 玛格威

作者 Lesley Koyi

插图 Wiehan de Jager

译文 Dawit Girma

配音 Abenezer Chane

语言 阿姆哈拉语

级别 5级

将整故事念出来

播放速度

自动念故事


በተጨናነቀችው የናይሮቢ ከተማ በርካታ የጎዳና ተዳዳሪዎች ይኖራሉ። የስቃይ ኑሮ በየእለቱ ይገፋሉ፤ እያንዳንዱን ቀን አንዲሁ ይቀበሉታል። አንድ ቀን ጠዋት ልጆቹ ከመንገድ ዳር የተኙበትን ምንጣፍ ጠቀለሉ። ብርዱን ለመከላከል ቆሻሻ አንድደው እሳት ይሞቁ ነበር። ከልጆቹ ውስጥ ማጎዝዌ በእድሜ ትንሹ ነበር።

在内罗毕这座繁忙的城市里,住着一群流浪的男孩,他们日复一日地活着,从来不知道什么是舒适安逸的生活。一天早上,男孩们从冰冷的人行道上醒来,把他们用来睡觉的毯子叠起来。天太冷了,为了驱赶寒气,他们用拾来的垃圾燃起了一堆火。在这群男孩中有一个人叫玛格威。


ወላጆቹ ሲሞቱ ማጎዝዌ ገና 5 ዓመቱ ነበር። ከአጎቱ ጋር ለመኖር ሄደ። አጎትዬው ግን ለልጁ አያስብለትም ነበር። ለማጎዝዌ በቂ ምግብ አይሰጠውም። ከባባድ ስራዎች ያሰራው ነበር።

玛格威的父母过世时,他只有五岁,他搬去跟叔叔一起生活。叔叔从来不关心玛格威。玛格威在叔叔家挨饿受冻,还要干很多体力活。


ማጎዝዌ ካማረረ ወይ ጥያቄ ከጠየቀ አጎቱ ይገርፈዋል። ትምህርት ቤት ለመሄድ ሲጠይቅ አጎቱ ይመታውና እንዲህ ይላል፣ ‹‹አንተ በጣም ደደብ ነህ ምንም መማር አትችልም›› በእንዲህ አይነት ሁኔታ ሶስት ዓመታት ከቆዬ በኋላ አንድ ቀን ሮጦ ከአጎቱ አመለጠ። ጎዳና መኖርም ጀመረ።

一旦玛格威稍有抱怨,叔叔就会对他拳打脚踢。有一次,玛格威问叔叔他能不能去上学,叔叔狠狠地打了他几下,说:“你这傻瓜,用得着上学吗?”玛格威过了三年这样的日子,终于离家出走,无家可归。


የጎዳና ህይወት በጣም አስቸጋሪ ሲሆን ልጆች ምግብ ለማግኘት በየቀኑ ሲለፉ ይውላሉ። አንዳንዴ ይታሰራሉ፣ አንዳንዴ ደግሞ ይገረፋሉ። ሲታመሙ የሚያሳክማቸው ማንም የለም። ልጆቹ ኑሯቸውን የሚገፉት በልመና እና የወዳደቁ እንደላስቲክ አይነት ነገሮችን በመሸጥ በሚያገኙት ትንሽ ገንዘብ ነው። ከከተማው ሌላ ሰፈር ካሉ ሌሎች ጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር የተሻለ ለማግኘት የሚያደርጉት ፉክክር ኑሯቸውን ይበልጥ ያመረዋል።

流浪生活非常艰辛,大多数男孩每天只能混个温饱。他们有时候会被抓起来,有时候会挨打。当他们生病的时候,没有人照顾他们。这群男孩就靠乞讨得来的一点点钱过活,他们有时候也会卖塑料品和旧货赚点钱。有时候别的流浪汉会来找茬,争夺领地,那时候生活就更艰难。


አንድ ቀን ማጎዝዌ የቆሻሻ ገንዳ ላይ እየፈለገ ሳለ አንድ የሆነ የተጎሳቀለና ያረጀ የተረት መጽሐፍ አገኘ። አጸዳዳውና በቦርሳው ከተተው። በየቀኑ መጽሐፉን ያወጣና ስእሎቹን ያያል። ማንበብ ግን አይችልም ነበር።

有一天,玛格威正在翻垃圾箱,他找到了一本破旧不堪的故事书。他把书上的灰尘吹走,把书放进了袋子里。每天完工后,他会把书拿出来,翻着上面的图画,可惜他看不懂上面的文字。


ስእሎቹ ስለአንድ አውሮፕላን አብራሪ መሆንን እየተመኘ ስላደገ ልጅ ይተርካል። ማጎዝዌ አውሮፕላን አብራሪ የመሆን ነገር እንደቅዠት ያልም ጀመር። በተረቱ ውስጥ ያለው ልጅ ታሪክ የእሱ ይመስለዋል።

图画书讲的是一个男孩长大成为飞行员的故事。玛格威有时候会梦想自己成为一个飞行员。有时候,他想象着自己就是故事中的男孩。


ቀዝቃዛ ነበር፤ ማጎዝዌም መንገድ ዳር ቆሞ ይለምናል። አንድ ሰው ወደእሱ እየተራመደ ሄደ። ‹‹ሰላም! ቶማስ እባላለሁ፣ እዚሁ አካባቢ ነው የምሰራው፣ አንተ ምግብ ማግኘት የምትችልበት ቦታ›› አለ ሰውየው። ቢጫ ቀለም ወደተቀባ ባለ ሰማያዊ ጣራ ቤት ጠቆመ። ‹‹ርግጠኛ ነኝ ወደዚያ ሄደህ ምግብ ትለምናለህ?›› ሰውየው ጠየቀ። ማጎዝዌ አንዴ ሰውየውን ቀጥሎ ደግሞ ቤቱን ተመለከተ። ‹‹ምናልባት›› አለ፤ ከዚያም ሄደ።

有一天,天气很冷,玛格威站在街头乞讨。一个男人走过来,跟他打招呼:“你好,我叫托马斯。我在这儿附近工作,你可以到那儿拿点吃的。”他指着一座蓝顶黄墙的房子,“我希望你别客气,到那儿去拿点吃的吧!”玛格威看了看男人,又看了看房子,说:“可能吧!”然后他就走开了。


በቀጣዮቹ ወራት ጎዳና ተዳዳሪዎቹ ልጆች ቶማስን በአካባቢው መመልከት ለመዱ። ቶማስ ከሰዎች ጋር ማውራት ይወዳል በተለይ ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር። ቶማስ የሰዎችን ታሪክና የህይወት ገጠመኝ ያዳምጣል። ቆፍጣናና ትእግስተኛ ነው፤ ትእቢተኛና ሰው የማያከብር አይደለም። አንዳንዶቹ ልጆች ወደ ቢጫና ሰማያዊው ቤት ምግብ ለማግኘት በእኩለ ቀን መሄድ ጀመሩ።

接下来的几个月,流浪的男孩们渐渐认识了托马斯。他喜欢跟人聊天,特别是无家可归的人。托马斯听别人讲他们的故事。他不苟言笑,非常耐心、有礼貌,尊重他人。一些男孩开始在白天去蓝顶黄墙的房子里找吃的。


ማጎዝዌ መንገዱ ዳር እግረኛ መንገድ ጥግ ሆኖ ባለስእል የተረት መጽሐፉን እየተመለከተ ሳለ ቶማስ መጥቶ አጠገቡ ተቀመጠ ። ‹‹ተረቱ ስለምንድን ነው?›› ቶማስ ጠየቀ። ‹‹አንድ ፓይለት ስለሆነ ልጅ ታሪክ ነው›› መለሰ ማጎዝዌ። ‹‹የልጁ ስም ማነው?›› ጠየቀ ቶማስ። ‹‹አላውቅም፤ ማንበብ አልችልም እኮ›› አለ ማጎዝዌ ለስለስ ብሎ።

有一天,玛格威正坐在人行道上看故事书,托马斯来了坐在他旁边。托马斯问:“这本书讲了什么故事?”玛格威回答说:“这是关于一个男孩成为飞行员的故事。”托马斯问:“男孩叫什么名字?”玛格威声音低了下去:“我不知道,我不识字。”


በተገናኙ ጊዜ ማጎዝዌ ታሪኩን ሁሉ ለቶማስ ያጫውተዋል። አጎቱ እንዴት እንዳደረገው እና እንዴት ማምለጥ እንደቻለ ይነግረዋል። ቶማስ ብዙ አያወራም፣ ማጎዝዌንም እንዲህ አድርግ እንዲያ አታድርግ አይልም፣ ዝም ብሎ በአትኩሮት ብዙ ያዳምጠዋል። አንዳንዴ ባለሰማያዊው ጣራ ትልቁ ቤት ምግብ ሲበሉም ያወራሉ።

当他们再次见面的时候,玛格威开始跟托马斯讲自己的故事,他的叔叔怎么对他,他怎么逃离了叔叔家。托马斯没说什么,也没有告诉玛格威该怎么做,但是他听得很仔细。有时候他们会一边在蓝顶黄墙的房子里吃东西,一边聊聊天。


የማጎዝዌ 10ኛ ዓመት ልደት ሲደርስ ቶማስ ለማጎዝዌ አዲስ የተረት መጽሐፍ ሰጠው። ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ስለሆነ በአንድ መንደር ይኖር ስለነበረ ልጅ ነበር ታሪኩ የሚያትተው። ቶማስ ይህን ታሪክ ለማጎዝዌ ብዙ ጊዜ አነበበለት፤ አንድ ቀን እንዲህ አለው፣ ‹‹እንደማስበው አሁን ትምህርት ቤት የምትገባበትና ማንበብ የምትማርበት ጊዜ ነው። ምን ታስባለህ?›› ቶማስ የልጆች ማቆያና ትምህርት ማግኘት የሚችሉበት ቦታ መኖሩን አብራራለት።

玛格威十岁生日的时候,托马斯给了他一本新的故事书,这是关于一个乡下男孩成为足球运动员的故事。托马斯给玛格威讲过这个故事很多次。有一天,托马斯说:“我觉得你应该去上学,去识字。你觉得呢?”托马斯说他知道一个地方,孩子们可以住在那儿,上学。


ማጎዝዌ ስለተጠቆመው አዲስ ቦታና ትምህርት ማግኘት ስለሚችልበት ሁኔታ ማሰላሰል ያዘ። አጎቱ ያለው ትክክል ቢሆንስ? ትምህርት መማር የማይችል በጣም ደደብ ቢሆንስ? እዚህ አዲስ ቦታ ከሄደ በኋላ ቢገርፉትስ? መፍራት ጀመረ። ‹‹ምናልባትም እዚሁ ጎዳና ላይ መሆን ሳይሻል አይቀርም›› ብሎ አሰበ።

玛格威想了想去新地方生活,上学。但是,如果他叔叔说得对,他太笨了上不了学怎么办?如果在新的地方,他又要挨打怎么办?他有点儿害怕,心想:“也许我注定就要睡在马路边。”


ስጋቱን ለቶማስ አጋራው። ከጊዜ በኋላ ቦታው ትክክለኛና የተሻለ መሆኑን ቶማስ አረጋገጠለት።

他把自己的想法告诉了托马斯。托马斯对他循循善诱,终于说服了玛格威,他在新地方一定会过上更好的生活。


ከዚያም ማጎዝዌ ባለአረንጓዴ ጣራ ቤት ውስጥ ወዳለ አንድ ክፍል ሄደ። ክፍሉን ከሌሎች ሁለት ልጆች ጋር ነው የተጋራው። በቤቱ ባጠቃላይ አስር ልጆች ይኖራሉ። አብረውም ሲሲ እና ባሏ፣ ሶስት ውሻዎች፣ አንዲት ድመት እንዲሁም አንድ ያረጀ ፍየል ይኖራሉ።

玛格威搬到了新家,新家的屋顶是绿色的。他和两个男孩住一间房间。屋子里还住着其他十个孩子。和他们住在一起的是茜茜阿姨和她的丈夫,还有三只狗,一只猫,一头老山羊。


ማጎዝዌ ትምህርት ጀመረ፣ ግን ትምህርቱ ትንሽ አስቸጋሪ ሆኖበታል። አንዳንዴ ለማቋረጥ ሁሉ ይመኛል። ነገር ግን አየር አብራሪ እና ታዋቂ ኳስ ተጫዋች የሆኑትን በተረቱ ውስጥ ያሉትን ልጆች ያስባል። ልክ እንደነሱ ትምህርቱን ማቋረጥ የለበትም፣ እነሱ እንደሆኑት ሁሉ ያሰበበት መድረስ ይችላል።

玛格威开始读书,他遇到了不少困难,很难赶上他的同学们,有时候他差点就要放弃了。但他每次想起故事书里的飞行员和足球运动员,他都坚持了下来,就像他们一样。


ባለአረንጓዴ ጣራው ቤት ግቢ ውስጥ ቁጭ ብሎ ከትምህርት ቤት የወሰደውን የተረት መጽሐፍ ያነባል። ቶማስ መጣና አጠገቡ ተቀመጠ። ‹‹ተረቱ ስለምን ነው?›› ቶማስ ጠየቀ። ‹‹ታሪኩ አንድ መምህር ስለሆነ ልጅ ነው።›› ማጎዝዌ መለሰ። ‹‹የልጁ ስም ማነው?›› ጠየቀ ቶማስ። ‹‹ስሙ ማጎዝዌ ይባላል!›› አለ ማጎዝዌ በፈገግታ።

有一天,玛格威正在屋子后院里看书,托马斯来了,坐在他旁边:“这本书讲了什么故事?”玛格威回答说:“这是关于一个男孩变成老师的故事。”托马斯问:“那个男孩叫什么名字?”玛格威咧嘴一笑:“他叫玛格威。”


作者: Lesley Koyi
插图: Wiehan de Jager
译文: Dawit Girma
配音: Abenezer Chane
语言: 阿姆哈拉语
级别: 5级
出处: 原文来自非洲故事书Magozwe
共享创意授权条款
本着作系采用共享创意 署名 4.0 未本地化版本授权条款授权。
读多啲5级故事:
选项
返回故事列表 下载 PDF